1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድሪምላይነር አውሮፕላን በረራ መጀመሩ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 22 2005

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ3 ወራት ያህል ከመሬት እንዳይነሳ በመላው ዓለም ታግዶ የቆየውን ድሪም ላይነር አውሮፕላን በማስነሳት ተሳፋሪዎችን ጭኖ መደበኛ በረራ አካሄደ። ጃፓን ድሪምላይነር አውሮፕላን ላይ ሰው ከማሳፈሯ አስቀድሞ መንገደኞች ያልተጫኑበት ከ200 በላይ የበረራ ሙከራዎችን እንደምታደርግ ጠቅሳለች።

https://p.dw.com/p/18PrT
ቦይንግ 787 አውሮፕላን የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ
ቦይንግ 787 አውሮፕላን የኢትዮጵያ ዓየር መንገድምስል Reuters

ድሪም ላይነር ቦይንግ 787 ግዙፍ አውሮፕላን ገጠመው በተባለው የባትሪ ችግር ምክንያት ነበር ከመሬት እንዳይነሳ ታግዶ የቆየው። ባሳለፍነው ቅዳሜ ግን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህን ለ3 ወራት ያህል ከመሬት እንዳይነሳ በመላው ዓለም ታግዶ የቆየውን ድሪም ላይነር አውሮፕላን ማብረሩ ተዘግቧል። ለመሆኑ አየር መንገዱ ሰዎችን ጭኖ ከዓለም በቀዳሚነት መደበኛ በረራውን ለማካሄድ ምን አነሳሳው? በረራውስ በምን መልኩ ነበር የተጠናቀቀው? ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ በኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የበረራ መምሪያ ኃላፊ፥ ካፒቴን ደስታ ዘርዑን አነጋግሬያቸው ነበር፤ የሚከተለውን መልስ በመስጠት ይንደረደራሉ።


ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ