1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድርቅና የእርዳታ ጥሪ

ሰኞ፣ መጋቢት 12 2008

በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች ዉስጥ የተከሰተዉን ድርቅ በሚመለከት ተደጋጋሚ ዓለም አቀፍ የርዳታ ጥሪዎች ተደርገዋል። እስካሁን ለችግር የተጋለጠዉ ሕዝብ ከ10 ሚሊየን በላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የእርዳታ ድርጅቶች ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችልም ያሳስባሉ።

https://p.dw.com/p/1IH42
USAID PK in Addis Abeba Äthiopien
ምስል DW/G.Tedla HG

[No title]

። የሀገሪቱ መንግሥትም ከፍተኛ ገንዘብ ለዚሁ ተግባር መመደቡን አስታዉቋል። ከለጋሾች በድርቁ የተጎዱትን ለመርዳት ከፍተኛ የገንዘብ እርዳታ ያቀረበችዉ ዩናይትድ ስቴት ስትሆን የሀገሪቱ የዉጭ አስቸኳይ የእርዳታ ድርጅት USAID ኢትዮጵያ ዉስጥ የባለሙያዎች ቡድን አሠማርቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ከ50ዓመታት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ በተባለዉ ድርቅ የተጎዱትን ወገኖች ለመርዳት ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። የዓለም አቀፍ ለጋሾች እርዳ መዘግየቱን ያመለከተዉ የኢትዮጵያ መንግሥትም ለጋሾች አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጡ አሳስቧል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ