1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድርቅ፣ ረሃብና የአገር በቀል አዝርእት፣

ረቡዕ፣ ሐምሌ 20 2003

የመንግሥታት መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ የገንዘብና የግብርና ተቋማት ፤ የመንግሥት ያልሆኑ የግብረ-ሠናይ ድርጅቶችና በሰብአዊ እርዳታ ላይ ያተኮሩ ታዋቂ ዓለም አቀፍ የኪነ ጥበብ ሰዎች፤

https://p.dw.com/p/RcdG
ምስል AP

በድርቅ ሳቢያ በመራብ ላይ ላለው የምሥራቃዊው አፍሪቃም ሆነ የአፍሪቃው ቀንድ ህዝብ፤ ለጊዜው፤ አያሌ ሜትሪክ ቶን እህልና የበሰለ ምግብ እንዲቀርብለት በመማጸን ላይ ናቸው።

ድርቅን ለመቋቋም ፤ ረሃብንም ለመታገል፣ ለዘለቄታው፤ የአገር አቀፍ የሰብል አዝርእትንና ዕጽዋትን ጠቀሜታም ሆነ ድርሻን፤ አያያዝንም በተመለከተ ሳይንቲስቶች ምን ይላሉ? ሳይንስና ኅብረተሰብ ዝግጅታችንን ይከታተሉ---

በአሁኑ ወቅት፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰፊው የመወያያ አርእስት ከሆኑት ጥቂት ዐበይት ጉዳዮች አንዱ፤ ከ 60 ዓመታት ወዲህ ምሥራቃዊውን አፍሪቃ፣ ኢትዮጵያን ጭምር እጅግ ክፉኛ እንደመታ የሚነገርለት ድርቅና ረሃብ ነው። በድርቁ ሳቢያ ፤ ለረሃብ የተጋለጠው 12 ሚሊዮን ያህል ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንዲደረግለት ተማጽኖ እየቀረበ ነው። በሰሜናዊው ኬንያ ፤ ቀቢፀ-ተስፋ ያደረባቸው አርብቶ አደሮች፤ ከብቶቻቸው በውሃና በእሳር እጦት እየተሰቃዩ ከሚሞቱ ቢገላገሉ ይሻላል በማለት መግደል መጀመራቸው እየተነገረ ነው። ረሃብንና ድርቅን ለመቋቋም ፣መላው፣ ምን ይሆን? የሥነ-ፍጥረት ጠበብት ምን ይላሉ? በአገር-በቀል የእህል ዘር ፤ ሰፊ ምርምር በማድረግና እንዲጠበቅም ባደረጉት አስተዋጽዖ የታወቁት ፣ Right Livelihood Award የሚሰኘው የአማራጩ የኖቤል ሽልማት ባለቤት ፣ ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት--ዶ/ር መላኩ ወረደ---

(ድምፅ) «ዋናው ጉዳይ-----------------------ማጎልበት!»

ተገን ወይም አለኝታ ያሏቸው ፣ አገር በቀል አዝርእት፣ እንዲሁም ዕጽዋት ያላቸው ጠቀሜታ በቀላሉ የሚታይ አይሆንም። በመሆኑም እነርሱ የሚስፋፉበትንና የሚጠበቁበትን

ሁኔታ ማጎልበት የግድ የሚል መሆኑን ዶ/ር መላኩ ይናገራሉ፣ ይመክራሉ። ማጎልበት ሲባል በትክክል ምን ማለት ይሆን?---

(ድምጽ)----ማጎልበት ሲባል--እርምጃ መውሰድ ነው።»

ጤፍ ፤ማሽላ ፤ ስንዴ፤ ገብስ፤ ባቄላ፤ አተር፣ ሌሎች ሌሎችም የኢትዮጵያ አገር በቀል አዝርእት ምርታማናታቸው እንዴት ነው ሊጨምር የሚችለው? የምርቱ መጠን ከፍ እንዲል ለማድረግ ምን ዓይነት ሳይንሳዊ እርምጃ መውሰድ ይቻላል?

(ድምጽ)«-------------------------»

አገር በቀል አዝርእትና ዕጽዋት እንዲስፋፉና እንዲጠበቁ ከመንግሥትና ከተለያዩ የመንግሥትም ካልሆኑ የግብርና ድርጅቶች ያገኘው ድጋፍ እስከምን ድረስ ነው ይላሉ? የቱን ያህል ትኩረት ተሰጥቶታል?

ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ