1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዶክተር አምባቸው መኮንን ተሾሙ

ቅዳሜ፣ የካቲት 30 2011

ተሰናባቹ አቶ ገዱ ለምክር ቤቱ ባሰሙት ንግግር የአማራ ክልል ህዝብ ከሌሎች ብሔረሰቦች ጋር የቆየውን ትስስር እንዲያጠናክር ጠይቀዋል። የአማራ እና የትግራይ ህዝብን አንድነት ለማፍረስ የሚደረጉ ሙከራዎችም እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/3Egf4
Äthiopien l Dr Ambachew Mekonnen
ምስል DW/A. Mekonnen

የአማራ ክልል መስተዳድር አዲስ ፕሬዝደንት ሾመ

ዶክተር አምባቸው መኮንን በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነት ዛሬ ቃለ መሀላ ፈጸሙ። የአማራ ክልል ምክር ቤት 12ኛ መደበኛ ጉባዔ ክልሉን ሲመሩ የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ያቀረቡትን የሥራ መልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሎ ዛሬ በምትካቸው ዶክተር አምባቸውን በርዕሰ መስተዳድርነት ሾሟል። ተሰናባቹ አቶ ገዱ ለምክር ቤቱ ባሰሙት ንግግር የአማራ ክልል ህዝብ ከሌሎች ብሔረሰቦች ጋር የቆየውን ትስስር እንዲያጠናክር ጠይቀዋል። የአማራ እና የትግራይ ህዝብን አንድነት ለማፍረስ የሚደረጉ ሙከራዎችም እንዲቆሙ ጠይቀዋል። አለምነው መኮንን ከባህርዳር ዝርዝሩን ልኮልናል። 
አለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ