1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀሃዳዊ ሃረካት ዘጋቢ ፊልምና ተቃዉሞው

ሐሙስ፣ ጥር 30 2005

መንግስት በአሸባሪነት ወንጀል ክስ የመሠረተባቸዉ የ29ኙ ሙስሊም ተከሳሾች የፍርድ ሂደት ያዛባል የተባለዉን እና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ማክሰኞ ምሽት ማሳየት የጀመረዉን ጀሃዳዊ ሃረካት የሚል ርዕስ የተሰጠዉ ዘጋቢ ፊልም እንዳይታይ የተከሳሾቹ ጠበቆች ለፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረባቸዉ ተሰምቷል።

https://p.dw.com/p/17aVW
ምስል AP

በ29ኙ ተከሳሾች ላይ የሚቀርበዉን ምስክርነት በዝግ የሚመለከተዉ ፍርድ ቤት የተባለዉ ፊልም እንዳይታይ ማገዱንም ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል። እንዲያም ሆኖ ዘጋቢዉ ፊልም መታየቱ አልቀረም። የዘጋቢ ፊልሙ መቅረብ የሙስሊሙን ጥያቄ ሊያዳፍን አይችልም ሲል አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ መግለጫ አዉጥቷል፤ የተከሳሾች ጠበቆች አቤት ባሉት መሰረትም ፍርድ ቤት ለነገ ጉዳዩን እንደሚያይ ተሰምቷል። ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔርን በዚህ ጉዳይ ላይ ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ በአጭሩ አነጋግሬዋለሁ።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ