1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመናዊ ዲዛይነር ካርል ላገርፌልድ አረፈ

ማክሰኞ፣ የካቲት 12 2011

በፋሽኑ ዓለም ስሙ የገነነው ጀርመናዊ የዘመናዊ የልብስ ቅድ ባለሞያ ዲዛይነር ካርል ላገርፌልድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ላገርፌልድ ዛሬ  በ85 ዓመቱ ማረፉን የርሱ ፋሽን መለያ የሆነው ሻኔል አረጋግጧል። ላገርፌልድ ከጎርጎሮሳዊው 1983 ዓም ጀምሮ በሚመራው በፓሪሱ የሻኔል የልብስ ፋሽን ትርዒት ላይ ከአንድ ወር ወዲህ መታየት አቁሞ ነበር።

https://p.dw.com/p/3Dgd1
Karl Lagerfeld
ምስል Getty Images/A. Weiss

በፋሽኑ ዓለም ስሙ የገነነው ጀርመናዊ የዘመናዊ የልብስ ቅድ ባለሞያ ዲዛይነር ካርል ላገርፌልድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ላገርፌልድ ዛሬ  በ85 ዓመቱ ማረፉን የርሱ ፋሽን መለያ የሆነው ሻኔል አረጋግጧል። ላገርፌልድ ከጎርጎሮሳዊው 1983 ዓም ጀምሮ በሚመራው በፓሪሱ የሻኔል የልብስ ፋሽን ትርዒት ላይ ከአንድ ወር ወዲህ መታየት አቁሞ ነበር። ከፈረንሳዩ ሻኔል በተጨማሪ ላገርፌልድ ለኢጣልያው ፌንዲም ይሰራ ነበር። በፋሽኑ ኢንዱስትሪ የተሰማሩ ባለሞያዎች እና አድናቂዎቹ በላገርፌልድ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ነው። ላገርፌልድ  ፀጉሩን በፖኒቴል በማስያዝ እና ከዓይኑ በማይለየው ጥቁር መነጽር ይታወሳል።

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ