1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን:መርዛማዉ የከብቶች መኖና ሥጋቱ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 28 2003

ዳዮክሲን ወይም በጀርመንኛዉ ዲዮክሲን የተባለዉ መርዛማ ንጥረ ነገር በተለይ እንቁላልና ሥብ ሥጋ የሚመገቡ ሰዎችን ለአደገኛ ነቀርሳ ወይም ካንሰር እንደሚዳርግ የጤና ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ

https://p.dw.com/p/QoL6
አደጋምስል picture-alliance/dpa

መርዛማዉ የከብቶች መኖና ሥጋቱ


ጀርመን ዉስጥ የዶሮና የሌሎች እንስሳት መኖ የሚያዘጋጁ ፋብሪካዎች ከመኖዉ ጋር መርዛማ ንጥረ ነገር መቀላቀላቸዉ የሐገሪቱን ፖለቲከኞችና እንስሳ አርቢዎችን አስቆጥቷል።ከመኖዉ ጋር የተቀላቀለዉ ዳዮክሲን ወይም በጀርመንኛዉ ዲዮክሲን የተባለዉ መርዛማ ንጥረ ነገር በተለይ እንቁላልና ሥብ ሥጋ የሚመገቡ ሰዎችን ለአደገኛ ነቀርሳ ወይም ካንሰር እንደሚዳርግ የጤና ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።ጉዳዩ ባደባባይ መነገር ከጀመረበት ጀምሮ አብዛኛዉ ሕዝብ እንቁላልና ሥጋ መመገቡን አቁሟል።ይሕ ደግሞ እንስሳ አርቢዎችንና ነጋዴዎች እያከሰረ ነዉ።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል ዝርዝሩን ልኮናል።

ይልማ ሐ/ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ