1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመንና የምርጫ ዝግጅት፣

ሰኞ፣ ሚያዝያ 7 2005

በጀርመን ፤ በመጪው ዓመት መግቢያ ማለትም መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ ም አጠቃላይ የፌደራል ም/ቤታዊ ምርጫ ይካሄዳል። በሄሰን ፌደራል ክፍለ ሀገር ደግሞ፣ በተጨማሪ የክፍለ ሀገር ም/ቤታዊ ምርጫ ነው የሚከናወነው። አሁን በሥልጣን ላይ ያሉት

https://p.dw.com/p/18GM6
ምስል ERIC FEFERBERG/AFP/Getty Images

ተጣማሪ ፓርቲዎች CDU/CSU እና FDP እጩ ተወዳዳሪ አሁንም ራሳቸው መራኂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ሲሆኑ፣ ከዋናው ጠንካራ የተቃውሞ ፓርቲ (SPD)የቀድሞው የገንዘብ ሚንስትር ፔር እሽታይንብሩክ መሆናቸው የታወቀ ነው።

ከታላላቆቹ ፓርቲዎች ሌላ ድምፅ የሚሻሙ ፤ የሥልጣኑን ሚዛን ይበልጥ ለአንዱ ወገን እንዲደፋ የሚያደርጉ አዳዲስ ፓርቲዎች በየጊዜው ብቅ ማለት ይዘዋል። አማራጭ ፈለግ እከታላለሁ የሚለውና ፣ ጀርመን ከዩውሮ ማኅበር እንድትወጣ ዋና ዓላማ አድርጎ የተነሣው ፓርቲ ነው። ስለ ፓርቲዎች አሰላለፍና ስለምርጫ ዝግጅት የበርሊኑን ዘጋቢአችንን ይልማ ኃ/ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬው ነበር።

ይልማ ኃ/ሚካኤል

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ