1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመንና ፈረንሳይ ግንኙነታቸዉን እንደሚያጠብቁ ገለፁ

ሐሙስ፣ የካቲት 21 2011

ጀርመንና ፈረንሳይ ግንኙነታቸዉን እንደሚያጠብቁ ገለፁ። ሁለቱ ጎረቤታምና ወንድማማች ሃገራት በወታደራዊና በኢኮኖሚዉ ዘርፍ ያሉት ስምምነቶችን ይበልጥ ተግባራዊ ለማድረግ ይበልጥ እንደሚሰሩ ሁለቱም መሪዎች በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/3EGpL
Frankreich, Paris: Staatsbesuch Angela Merkel trifft Emmanuel Macron
ምስል Reuters/G. Fuentes

የጀርመን እና የፈረንሳይ የበለጠ ግንኙነት እና ትስስር አዉሮጳን ይበልጥ ወደፊት ሊያራምዳት የሚችል እንደሚችል ተገለፀ ። ይግ የተነገረዉ ትንናት ፓሪስ ላይ የየጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት አማኑኤል ማክሮ በሁለቱ ሃገራት ግንኙነት እና የትብብር ስምምነቶች እንዲሁም በአዉሮጳ እና በአለም አቀፍ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመከሩ ጊዜ ነዉ። ሁለቱ ጎረቤታምና ወንድማማች ሃገራት በወታደራዊና በኢኮኖሚዉ ዘርፍ ያሉት ስምምነቶችን ይበልጥ ተግባራዊ ለማድረግ ይበልጥ እንደሚሰሩ ሁለቱም መሪዎች በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል። ቦታዉ ላይ የተገኘችዉ የፓሪስዋ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝር ዘገባዉን ልካልናለች።

 

ሃይማኖት ጥሩነህ

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ