1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን ለየመን 100 ሚሊዮን ይሮ ርዳታ ልትሰጥ ነዉ

ማክሰኞ፣ የካቲት 19 2011

የጀርመን ፌደራል መንግሥት የተመድ የመንን ለመርዳት በሚያደርገዉ ጥረት 100 ሚሊዮን ይሮ ድጋፍ እንደሚሰጥ ገለፀ። ይህን የገለፁት የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃይኮ ማስ ዛሬ ጄኔቭ ስዊዘርላንድ ላይ በተካሄደዉ ለየመን የርዳታ ማሰባሰብያ ጉባዔ ላይ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3E8bb

Die schweizerische Vizepräsidentin Simonetta Sommaruga, die schwedische Außenministerin Margot Wallström, der Generalsekretär der Vereinten Nationen, Antonio Guterres, und der Vize-Generalsekretär der Vereinten Nationen für humanitäre Angelegenheiten und Nothilfekoordinator Mark Lowcock
ምስል Getty Images/F. Coffrini

የጀርመን ፌደራል መንግሥት የተመድ የመንን ለመርዳት በሚያደርገዉ ጥረት 100 ሚሊዮን ይሮ ድጋፍ እንደሚሰጥ ገለፀ። ይህን የገለፁት የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃይኮ ማስ ዛሬ ጄኔቭ ስዊዘርላንድ ላይ በተካሄደዉ ለየመን የርዳታ ማሰባሰብያ ጉባዔ ላይ ነዉ። በጉባዔዉ ላይ ለየመን እስካሁን 2,3 ቢሊዮን ይሮ መሰብሰቡ ተመልክቶአል። የተሰበሰበዉ ገንዘብ አምና ከተሰበሰበው ርዳታ 30 በመቶ ይልቃል ተብሏል።  የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተረሽ የየመን ግጭት እጅግ የከፋ ሰብአዊ ቀውስ መፍጠሩን ተናግረዋል። የተመድ በዚህ ዓመት ብቻ ለየመን 3,7 ቢሊዮን ይሮ እንደሚያስፈልገዉ ይፋ አድርጓል።  በየመን 24 ሚሊዮን ነዋሪ የአስቸኳይ ርዳታ ጥገኛ ነዉ። 

 

አዜብ ታደሰ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ