1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን፣ ናሚቢያ እና የራስ ቅሎች ርክክብ ሥነ ሥርዓት

ቅዳሜ፣ መስከረም 20 2004

አንድ የናሚቢያ የልዑካን ቡድን ሰሞኑን ወደ በርሊን መጥቶ ነበር።

https://p.dw.com/p/Rome
በጀርመን የናሚቢያ የቅኝ አገዛዘ ዘመን የተገደለ የአንድ የሄሬሮ ተወላጅ የራስ ቅልምስል picture-alliance/dpa

የልዑካኑ ቡድን የበርሊን ጉዞ ዓላማ ጀርመናውያን ደቡብ ምራብ አፍሪቃዊቱን ሀገር በቅኝ ግዛት ይዘው በነበረበት ጊዜ በሄሬሮ እና በናማ ብሔረ ሰቦች አንጻር ባካሄዱት የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ የተገደሉ እና በኋላም ለምርምር ወደ በርሊን ተልከው ከነበሩ የሄሬሮ እና የናማ ብሔረ ሰቦች አባላት የራስ ቅሎች መካከል ሀያዎቹን ለመረከብ ነበር። የራስ ቅሎች በትናንቱ ዕለት በይፋ ሥነ ሥርዓት ለናሚቢያ መመለሳቸው እርግጥ በናሚቢያ እና በጀርመን ግንኙነት ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ ያሳርፋል ተብሎ ቢታሰብም፡ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ሀቀኛው ዕርቀ ሠላም በሚወርድበት ሁኔታ ላይ ግን የመጀመሪያውን ንዑሱን ድርሻ ብቻ እንዳበረከተ ነው የተገመተው።

ካይ አሌግዛንደር ሾልስ

አርያም ተክሌ

መሥፍን መኮንን