1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አያቅተንም፣ እንወጣዋለን

ሰኞ፣ ነሐሴ 16 2008

የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል «አያቅተንም፣ እንወጣዋለን» ያሉበት አነጋገራቸው ዓለምን አስደንቆአል፡፡ አሁን ብዙ ጥያቄዎችን በእሳቸውም ላይ አሰነስቶአል፡፡ ያለፈው አመት ቻንስለሩዋ ወይዘሮ አንጌላ ሜርክል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች አገራቸውን ጥለው ባሕር እና በረሃ አቋረወጠው አውሮጳ ደርሰዋል።

https://p.dw.com/p/1Jmsz
1608-19-DW-Wir-schaffen-das-Teaser-DEU.png

ግሪክ፣ ባልካንና ሐንጋሪ ድንበር ላይ በቀዝቃዛው የክረምት ወራት የደረሱት ስደተኞች የገጠማቸውን ችግር የተመለከቱት አንጌላ ሜርክል ያኔ ጀርመን ስደተኞቹን እንደምትቀበል ጥሪአቸውን አሰምተው ነበር፡፡
ይህ የማይረሳ ውሳኔአቸው በጀርመን አኳያ በዓለም የነበረውን ገጽታ እንደ አለ ቀይሮታል፡፡ብዙዎቹ በእርምጃው ተደንቀዋል፡፡ሌሎቹ ተገርመዋል፡፡ ጥቂት ተቺዎችንም አሰነስቶባቸዋል፡፡
ሜርክልም ስደተኞቹን የማስተናገዱን ስራ ባንድነት እንወጣዋለን፣ አንድ ላይ ሆነንም እንፈታዋለን… „ ብለው ሕዝቡን አበረታተው ነበር፡፡
እርምጃው በሰብዓአዊነቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ሥራ ነው፡፡
ግን አሁን ከአንድ አመት በኋላ „…አብረን እንወጣዋለን፣…አንድ ላይ ሆነን እንፈታዋለን…“ የሚለው የቻንሰለሩዋ ቃል ሌላም ችግር ውስጥ አስገብቷቸዋል።
የሜርክል ተቃዋሚዎች ብቻ ሳይሆኑ የረጅም ጊዜ የፖለቲካ ወዳጆቻውም ሳይቀሩ በቻንሰለሩዋ ላይ ተነስተውባቸዋል፡፡
በዚያም ላይ ስደተኞቹን እዚህ ለማስተናገድ ቢያንስ በአመት 20 ቢሊዮን ዩሮ ወጪ ማድረግ ያስፈልጋል የሚለው የገንዘብ ጥያቄም አብሮ ተነስቶአል፡፡
እዚህ ደርሰው፣ ተገን ለጠየቁት ስደተኞች ምን ያህል ብር ወጪ አድርጎ እነሱን ማስተናገድ ይቻላል፣የሚለውን ጥያቄ እዚህ ጀርመን አገር ለመመለስ በጣም አስቸጋሪም ሁኖአል፡፡ ትክክለኛ ቁጥራቸው እንኳን ምን ያህል እንደሆነ፣ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ከመስከረም ወር 2015 እ.አ.አ. እስከ ሐምሌ 2016 ድረስ ኮምፒውተር ላይ የተመዘገቡት ስደተኞች ቁጥር 900.623 ሺህ ሰዎች ናቸው፡፡ ይህን ቁጥር እራሱን ትክክል ነው ብሎ ለመቀበልም ያስቸግራል፡፡ምክንያቱም ያኔ በጥድፊያና በግርግር በእጃቸው የያዙት የመታወቂያ ወረቀታቸውም በደንብ ሳይጣራና ሳይመረመር፣ማንነታቸው በትክክል ሳይመዘገብ እዚያው በዚያው ቶሎ ተብሎ ተሰብስቦ ወረቀት ላይ የሠፈረ አኃዝ ነው፡፡፡
„እንደዚህ ዓይነቱ የጥድፊያ ሥራ ደግሞ አለጥርጥር“- የስደተኞችን ጉዳይ እዚህ እንዲከታተል በጀርመን መንግሥት የተሰየመው መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ እንዳሉት-፣ ግድፈትን ያጋጥመዋል፣ ከዚያም አልፎ አንድን ሰው ሁለት ጊዜ እሰከ መመዝገብ ድረስም የሚሄድ ስህተት ሊያመጣ ይችላል፡
„ ከእነዚህ ከተመዘገቡት ሰዎች ውስጥም ምን ያህሎቹ እዚህ ጀርመን አገር እንደቀሩ ወይም አገሩን ጥለው ወደ ሌላ ቦታ እንደተንቀሳቀሱ በተጨባጭ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ችግሩ ያለው ገና እንደ ደረሱ ከመጀመሪያው በሥነ-ሥርዓቱና በደንቡ አለመመዝገባቸው ነው፡፡“
አንድ የሚታወቅ ነገር ቢኖር፣ በዚህ በያዝነው አመት ጀርመን የገቡ የስደተኞች ቁጥር ከአለፈው አመት በጣም ዝቅ ያለ ነው፡፡
በሰኔ ወር 16 ሺህ 300 ሰዎች ነበሩ፡፡በጥር ወር እዚህ ደርሰው ተገን የጠየቁ ስደተኞች ቁጥር 91 ሺህ 600 ሰዎች ነበሩ፡፡
ወጣ ወረደ እዚህ የደረሱትን ለማስተማር፣ሥራ ለመስጠት፣የመኖሪያ ቤቶች ለማዘጋጀት፣የሕክምና ወጪዎቻቸውን ለመሸፈን፣ ምግባቸው፣ ልብሳቸው…ይህ ሁሉ በቢሊዮን የሚቆጠር ወጪን የሚጠይቅ ነው፡፡

Erfurt Messe Ankunft der Flüchtlinge im Herbst 2015
ምስል picture-alliance/dpa/M. Schutt
Deutschland Merkel und Seehofer
ምስል Getty Images/S. Gallup

አንድሪያስ ቤከር/ይልማ ኃይለሚካኤል

አርያም ተክሌ