1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን እና የፀጥታው ጥበቃ ርምጃ

ረቡዕ፣ ኅዳር 8 2008

በጀርመን እና በኔዘርላንድስ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድኖች መካከል ትናንት ሊካሄድ የነበረው ግጥሚያ በፀጥታ ስጋት መሰረዙ ይታወሳል። ይህንን ውሳኔ ያስተላለፉት የጀርመን አገር አስተዳደር ሚንስቴር እና ግጥሚያው ሊደረግባት የነበረችው የሀኖፈር ከተማ ፖሊስ ናቸው።

https://p.dw.com/p/1H7ww
Absage Fußball Länderspiel Deutschland Niederlande
ምስል picture-alliance/dpa/J. Stratenschulte

[No title]

የፓሪስን ጥቃት ተከትሎ፣ የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል፣ የሃገር አስተዳደሩ ሚንስትር ቶማስ ደ ሜዝየር እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለሽብርተኝነት እንደማይንበረከኩ ለማሳየት በሀኖፈር ስቴድየም በመገኘት ይከታተሉታል ተብሎ የተጠበቀው ጨዋታ ሊጀመር ጥቂት ጊዜ ሲቀረው ነበር ። ጨዋታውን መሰረዝ ለምን አስፈለገ? በተጨባጭ የታወቀ ጉዳይ አለ? የበርሊኑን ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል እንደሚከተለው አስረድቶዋል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ