1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን ዉህደት እና የምስራቅ ጀርመን ዘገምተኛ ለዉጥ

ዓርብ፣ መስከረም 23 2001

ምስራቅ እና ምዕራብ ጀርመንን ለያይቶ የነበረዉ ግንብ ፈርሶ ጀርመን ከተዋሃደ ሃያ አመታትን ሊያስቆጥር ሁለት አመት ነዉ የቀረዉ።

https://p.dw.com/p/FTVi
ምስራቅ እና ምዕራብ ጀርመንን ከፍሎ የነበረዉ ግንብ
በቅርቡ በወጣዉ ዘገባ መሰረት የቀድሞይቷ ምስራቅ ጀርመንን ከምዕራብ ጀርመን እድገት ጋር ያለዉን የኑሮ ደረጃ እኩል ለማድረግ ሌላ አስር አመታት ያስፈልጋል ተብሎአል። በምስራቅ ጀርመን መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት በርካታ ገንዘብ ወደ ምስራቅ ጀርመን ቢፈስም ክልሉ እስካሁን እራሱን ችሎ መቆም አልቻለም። በምስራቅ ጀርመን በርካታ የልማት መርሃ ግብሮች እንደተዘረጉ እና የግንባታዉ ስራ እንደተፋጠነ ነዉ የአካባቢዉ የግንባታ ሚኒስቴር ገለጻዉን የሚያቀርበዉ። በአሁኑ ወቅት ይህ መግለጫ ለምስራቅ ጀርመኑ ክፍል የህልም እንጀራ ያህል ነዉ ይላሉ፣ በጀርመን የትራንስፖርት እና የከተማ ልማት ሚኒሴር ዎልፍ ጋንግ ቲፍንሴ። በግንባታዉ ስራ በርካታ ነገሮችን አጠናቀናል ፣ ብዙ ነገሮችንም መስራት ይጠበቅብናል ይላሉ በማስከተል። መንግስት በየአመቱ ሰላሳ ሚሊያርድ ይሮ ለምስራቁ የጀርመን የግንባታ ስራ ከምእራቡ የጀርመን ክፍል ያስተላልፋል። ሌላዉ ምክንያት ደግሞ የምስራቅ ጀርመን ክፍል የሚኖሩ ህዝቦች የምጣኔ ሃብት ሁኔታ በምእራብ ጀርመን ከሚኖሩት ሲነጻጸር በአማካኝ ሰባ በመቶ ብቻ ነዉ። በዚህም ምክንያት የኢኮኖሚዉ ሁኔታ ማስተካከል አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ይላሉ የጀርመኑ የከተማ ልማት እና የትራንስፖርት ሚኒስቴር የቀድሞ የምስራቅ ጀርመን ክፍል ራሱን ለማስተዳደር እና በሁለት እግሩ ለመቆም ቢያንስ ተጨማሪ አስር አመት ያስፈልገዋል ።