1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ሊቀመንበር

ዓርብ፣ ሰኔ 24 2003

ጀርመን በዙር የሚደርሰዉን የተ.መ.ድ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የሊቀመንበርነትን ስልጣን ዛሪ ትረከባለች። በጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በያዝነዉ የጎርጎረሳዉያኑ የ2011አ.ም መጀመርያ ላይ ከሌሎች ዘጠኝ አገሮች ጋር አባልነትን የተመረጠችዉ ጀርመን እስከ ሚቀጥለዉ የጎርጎረሳዉያኑ 2012 አ.ም መጨረሻ ድረስ መምክር ቤቱ አባልነት ትቆያለች።

https://p.dw.com/p/RX8y
የተ.መ.ድ-ጀርመን አርማምስል DW Fotomontage

ከዛሪ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚዘልቀዉን የሊቀ መንበርነት ሃላፊነትዋንም ግጭት በሚካሄድባቸዉ አካባቢዎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታሎች ጥበቃ ለማድረግ የሚያስችሉ እርምጃዎችን የሚያስወግድ ግፊት ለማድረግ አቅዳለች። ስለዚሁ የዶቸ ቬለዋ ኒና ቬርክሆይዘር የዘገበችዉን አዜብ ታደሰ ታቀርበዋለች።

ጀርመን የተ.መ.ድ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ጉባኤ ለመጨረሻ ግዜ የተካፈለችዉ የኢራቁ ወረራ ሊጋጋም አፋፍ ደርሶ የካቲት ወር በጎርጎረሳዉያኑ 2003 አ.ም ላይ ነበር። በጉባኤዉ ኢራቅን ለመዉረር በቀረበዉ ሃሳብ የጀርመኑ የዛን ግዜዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮሽካ ፊሸር ለወረራዉ ነቀፊታን በማሳየታቸዉ ያልተጠበቀ ሁኔታን ነበር የፈጠረዉ።
የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በዘንድሮዉ ጉባኤዉም በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰቱ ዉጥረቶችን በሚመለከት በሚቀርበዉ አጀንዳ ላይ ዉሳኔዎችን ያሳልፋል። የተ.መ.ድ ሐምሌ ወር ላይ ከሚያካሂደዉ ጉባኤ ብዛኛዉን የሚመሩት በድርጅቱ የጀርመን አንባሳደር ፔተር ቪትግ ናቸዉ። ሃምሌ ዘጠኝ ነጻነትዋን በይፋ ስለምታዉጀዉ ደቡብ ሱዳን፣ በአረብ አገሮች ስለተቀሰቀሰዉ የፖለቲካ ስርነቀል ለዉጥ፣ ስለ አፍጋኒስታን ወቅታዊ ሁኔታ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ በዋናነት የሚነጋገርባቸዉ ነጥቦች መሆናቸዉን ተናግረዋል። ጀርመን ይላሉ ቪቲግ ምንም እንኳ ጀርመን በጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ በራስዋ ጥረት የምታቀርበዉን ሃሳብ የምታስፈጽምበት መድረክን ባታገኝም ጥረትዋን ትቀጥላች። ለምሳሌ ወደፊት ጦርነት በሚካሄድባቸዉ ቦታዎች ትምህርት ቤቶች ላይ ጥቃት እዳይጣል የሚከለክል የማዕቀብ ዉሳኔ ላይ እንዲደረስ አጠናክራ ትቀጥላለች። «የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ የህጻናትን መብት ለማስጠበቅ ተጨማሪ ዉሳኔ በማሳለፍ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጊዶ ቬስተር ቬለ ሃምሌ አስራ ሁለት እና ሃምሌ አስራ ሶስት ሲገኙ ኒዮርክ በተገኙበት ዉሳኔዉን እንዲጸድቅ እንፈልጋለን»
ተቀማጭነቱን ኒዮርክ ያደረገዉ የተ.መ.ድ ጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በልዪ ልዪ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር በየቀኑ ስብሰባ የሚጠራ ሲሆን አንዳንድ ግዜ በቀን ዉስጥ ሶስት አራት ግዜ ለስበሰብ ይችላል። ምክር ቤቱ አንድ ጉዳይ ላይ ዉሳኔ የሚያጸድቅ ከሆነ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት እና ግልጽ ስብሰባ ይካሄዳል። በሌላል በኩል አምስቱ የጸጥታ ምክር ቤቱ ቋሚ አባላት ተጠሪዎች እና አስሩ የምክር ቤቱ ቋሚ ያልሆኑ አባላት ተጠሪዎች ብቻም በዝግ ይሰበሰባሉ። የተ.መ.ድ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ፕሪዝደንት በየወሩ የሚመረጥ ሲሆን በአገሮች ስም የመጀመርያ ፊደል ተራ ቅደም ተከተል ምርጫዉ ይካሄዳል። ጀርመን ዛሪ የተቀበለችዉ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ የአንድ ወር የፕሪዝደንት ስልጣን ግዜዉ እጅግ አጭር ቢሆንም ብዙ ነገሮች የሚሰራበት ነዉ ይላሉ በተ.መ.ድ የጀርመን ማህበረሰብ ዋና ጸሃፊ ቢያተ ቫግነር
« ስልጣኑ የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ጉዳዮችን በመተግበር ራስ የሚፈትሽበት፣ በጸጥታ ምክር ቤቱ ምን አይነት ስልጣን አለ፣ ምን አይነት ሃላፊነትስ መወጣት ይኖርበታል፣ ነገሮችን እንዴት ወደ ጥሩ ፍጻሜ ማምጣት ይቻላል፣ የሚለዉን እና የወከሉትን አገር ገጽታ በግልጽ ማሳወቅ ላይ ነዉ። እናም ይህ ዋና እና አስፈላጊ ስራ ነዉ»
ጉባኤ መምራት፣ ማማከል፣ የያዙትን አጀንዳ ተከትሎ ጫፍ ማድረስ እና ጥሩ የዲፕሎማሲ ስራ የጸጥታ ምክር ቤቱ የአንድ ወር ሊቀመንበር ተግባራት ናቸዉ። ጀርመን በዲፕሎማሲ ክህሎትዋ ስመጥር በመሆንዋ በጸጥታዉ ምክር ቤት የስልጣን ግዜዋ ትልቅ እገዛን ያደርግላታል። ሆኖም በሊቢያዉ ቀዉስ ላይ የነበራት አቋም በጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የነበራትን ስም በትንሹም ቢሆን አጉድፎባታል። በተ.መ.ድ የጀርመን ማህበረሰብ ዋና ጸሃፊ ቢያተ ቫግነር እንደሚሉት በዚህ ረገድ ጀርመን በአጋሮችዋን ላይ ያልጠበቁት ሁኔታን ነዉ የፈጠረችባቸዉ!
ጀርመን በጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ በሊቢያ ጉዳይ ድምጸ ታቅቦ ማድረጓ በምክር ቤቱ ያላትን ደረጃ ዝቅ እንዳደረገባት አሁንም አትቀበለዉም። ምንም እንኳ ጀርመን በሶርያን ላይ የወሰደችዉ እርምጃ እንብዛም እገዛ ባይኖረዉም ምክር ቤቱ በሚያደርገዉ ዉሳኔ ላይ በከፍተኛ ደረጃ በመሳተፍ አብራ መስራት መፈለግዋን ግልጽ አድርጋለች። የደቡብ ሱዳን ሁኔታ ሌላዉ ጀርመን ትኩረት የምታደርግበት ጉዳይ ሲሆን ሃምሌ አጋማሽ ላይ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተርቬለ በጸጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ስም ደቡብ ሱዳንን በ193 ኛ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባልነት እንኳን ደህና መጣሽ ማለትን ይሻሉ። የተ.መ.ድ የጸጥታ ጥበቃዉ ምክር ቤትም የሱዳን ልዮ ሰላም አስከባሪ ጓድም ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን በይፋ ካወጀች ጀምሮ ልዪ እገዛዉን ይጀምራል።

Westerwelle Deutschland UN Sicherheitsrat
ጊዶ ቬስተርቬለምስል picture alliance / dpa
Peter Wittig Botschafter Deutschland UN Sicherheitsrat
ቪትግምስል picture-alliance/dpa

አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ