1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን የ2010 ሩ የአዉሮጻዉ የሙዚቃ ዉድድር አሸናፊ

ዓርብ፣ ግንቦት 27 2002

ሙዚቃ... ጀርመን የዘንድሮዉን የአዉሮጳ የሙዚቃ መድረክ ዉድድር አሸናፊ ሆና ህዝብ በደስታ ባንዲራውን ይዞ እያዉለበለበ በጋራ ዘምሯል።

https://p.dw.com/p/Ngqu
በኦስሎ፣ ኖርዌይ በተዘጋጀው የአውሮፓውያን የሙዚቃ ውድድር፤ በሰፊ ብልጫ ያሸነፈችው፤ የ 19 ዓመቷ ጀርመናዊት ተማሪ፤ ሌና ማየር-ላንድሩት፣ምስል EBU

ጀርመንን እወዳለሁ፣ ጀርመን እወዳለሁ ፣ጀርመን እወዳለሁ ብቻ ነዉ የሚለዉ ግጥሙ። ጀርመናዉያን ከሃያ ስምንት አመት በኋላ «ዩውሮ ቪዥን ሶንግ ኮንቴስት» በተሰኘ በአዉሮፓ የሚካሄደዉን የሙዚቃ ዉድድር ለሁለተኛ ግዜ በማሸነፋቸዉ እጅግ የተደሰቱበት ሁኔታም ነበር። ጤናይስጥልኝ አድማጮች፣ እንደምን ዋላችሁ፤ በዛሬው ዕለት ዝግጅታችን ባለፈዉ ቅዳሜ በኖርዌ ኦስሎ ስለተካሄደዉ የአዉሮጻ ሀገራት የሙዚቃ ዉድድር እናያለን፣

ሳተላይት ይሰኛል የአስራ ዘጠኝ ዓመትዋ ጀርመናዊት ባለፈዉ ቅዳሜ ፣ EROVISION SONG CONTEST በተሰኘዉ በአዉሮጳ በሚካሄደዉ የሙዚቃ ዉድድር ላይ አሸናፊ የሆነችበት የሙዚቃ።

ድምጽ ፩.የአሸናፊ

በኖርዊ ኦስሎ ላይ በተዘጋጀዉ በዚህ የሙዚቃ ዉድድር ላይ የአስራ ዘጠኝ አመትዋ ሌና ለዚሁ ለአዉሮጻዉ የሙዚቃ ዉድድር መድረክ ለመቅረብ በጀርመን አምስት ሽህ አዳዲስ ሙዚቀኞች በኦስሎ ለአዉሮጻዉያኑ የሙዚቃ ዉድድር ለመቅረብ ተወዳድረዉ ለማጣርያ አስራአምስት ተወዳዳሪዎች በቴሌቭዥን ስርጭት ሙዚቃቸዉን በማሳየት በየሳምንቱ ሙዚቃቸዉን በማቅረብ ህዝብ ስልክ በመደወል ጽንጽ ሰጥቶ ነዉ የጀርመን ህዝብ መርጧት ለአዉሮጻዉ የሙዚቃ ዉድድር የቀረበችዉ። ሌና ገና ለዉድድር ከመቅረብዋ ያላት ቀጥተኝነት ወጣት ነት እና መንፈሰ ጠንካራነት በጀርመናዉያን ህዝብ ዘንድ በጣሙን እንድትወደድ አድርጓትም ነበር። ሌና የጀርመንዋ አሽንፑትል ተብሎላታል ሰንደሪላ ለማለት ነዉ፤ በምንም ነገር ታዋቂ ያልነበረች ልጅ ከምንም ተነስታ ዝናዋ እና ዉበትዋ ስራዋ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያገኘች ለማለት። ሌና ማየር ላንድሩት በጀርመን ሃኖቨር ከተማ ነዋሪ ስትሆን እናትዋ ለቭቻቸዉ በጥሩ ያሳደግዋት እና ለዩንቨርስቲ ትምህርት በዝግጅት ላይ መሆንዋ ነዉ ስለግ ልህይወትዋ የተነገረዉ። ከዝያ በላይ እስዋም ሌና ራስዋ ስለግል ህይወትዋ በብዙሃን መገናኛ እንዲነገር እንደማትሻ ተአልጻል። ገና ለዉድድሩ ወደ ኦስሎ ኖርዊ ለመሄድ ስትነኣ ጀርመናዉያን እናእ ሌሎች የአዉሮያ አገሮች በተለይ በስዊዘርላንድ እና ሶስትርያ ሙዚቃዋ ተወዳጅነትን አግኝቶ ነበር። ጀርመናዉያኑም የሙዚቃ አዋቂዎችም ቅላጺዋ የእንግሊዘኛ አነጋገር እና አሰቧበርዋ እንደእንግሊዘኛ ተናጋሪ እንጂ አፉን በጀርመንኛ የፈታ ተናጋሪ አይነት አይደለም ብለዉ አስተያየታቸዉን በመስጠት ገልጸዉላታል። በሙሉ ልብ ወደ እስካንዲኒቢያ ያመራችዉ ሌላና ሙዚቃ ዉድድሩ ለመቅረብ ኦስሎ የማጣርያ ዉድድሩ ላይ ያዩዋት የሌላ አገር የሙዚቃ አፍቃሪዎችን ልብ ስባ በተለይ በኖርዊ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ማትረፍ ጀመረች፤ ነገር ግን አንዳንድ የእንግሊዝ ቋንቋ ተናጋሪ አገሮች እና ጋዜጠኞች የሌና ሙዚቃ ጥሩ ቢሆንም የእንግሊዘኛ ቋንቋ አነጋገርዋና አሰባበርዋ አስቂኝ ነዉ በነዉ የሚል ሹክሹክታን በመስማትዋ ለዉድድሩ ለመቅረብ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት በምትቀርብበት ቀን ዉድድሩን እንዳላሸንፍ የሚፈሩ ይሆናሉ በማለት ለዚህ ዉድድር ላበቃት እና ከመረጣት አለቃዋ ጋር በመሆን እሱ በጊታር እሷ በድምጽ ለደረሰባት ትችት ለጋዜጣዊ መግለጫ ስትቀርብ መልስ ሰጥች

ምንም አሉ ምም ጀርመናዉያን ጥሩ መቀለድ ጥሩ ማዜም ይችላሉ። ሳዜም የአነጋገር ዘይዩዩን ካለወዳችሁት ለማሻሻል የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ አሁንም አሻሻዪም ካልወደዳችሁት አሁንም ደግሜ እዘፍናለሁ በማለት እንግሊዘኛዉን ትንሽ ጠመም በማድረግ ነበር በማሹፍ ዘፍና ህዝብን ያሳቀችዉ። በአዉሮጻ እና በእዳንድ እስያ አገራት እንዲሁም ሜዲተራንያንን እና አዉሮጻን በሚያዋስኑ አገራት በቀጥጣ የቴሌቭዥን ስርጭት የተላለፈዉ የኡሮጻዉ የሙዚቃ ዉድድር መድረክ በግምት አንድነቶ ሃያ አምስት ሚሊዮን ተመልካች ስርጭሩን እነተከታተለዉ ተነግሮአል። የዘንድሮዉን ዉድድር ሃያ አምስት አገራት የተወዳደሩበት ሲሆን ጀርመን በሃያዉለተኛ ደረጃ ላይ ነበር በመድረክ የቀረበችዉ። ሰላሳ ዘጠኝ አገራት ደግሞ አሰኛፊ የሚሉትን አገር ስልክ እየደወሉ ድምጽ ሰጥተዋል። የኖርዌ ልኡላን እና ታዋቂ የአገሪቱ ፖለቲከቾች ሙዚቀኞች ጸሃፊዎች የተገኙበት እና በሽዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾች ባሉበት የቀረበዉ ዉድድር በመጨረሻም ጀርመን ድምጹ ድምጽን በማግኘት አሸናፊ ሆነች

NO FLASH: Eurovision 2010 - Lena (Germany wins ESC)
ምስል EBU

በጀርመን በቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት ይከታተለዉ የነበረዉ ጀርመናዊ ባንዲራዉን ይዞ ደስታዉን በመግለጽ መጨፈሩን ጀመረ የመገናኛ ብዙሃን መረሃግብሮቻቸዉን በኢስ በመቀየር የጀርመን አሸናፊነትን ማብሰር ዘፈኑ በየደቂቃዉ በስተጋባት ጀመረ። የእራ ዘጠነኝ አመቷን ወጣት ከሃያ ስምንት አመት በኻላ ድልን ያስገኘችልን ወጣትዋ ጀግናም ተባለላት፣ ወጣት ህጻን አዋቂዉ ደስታዉን ሲገልጽ ቆይቶ በነጋታዉ ጀርመንን በመወከል ወደ ኖርዊ የተጓዘችዉን ሌናን እና አጃቢዎችዋን ጭኖ እንዲያመጣ አንድ አዉሮፕላን ተልኮ ወደ ትዉልድ አገሯ ሃኖቨር ከተማ ይዞአት ተመለሰ። እሁድ አከቀኑ አስር ሰአት ላይ ዝናብ ይጥላል አዉሮፕላን ጣብያ ላናን ለመቀበል አስራአምስት ሽህ ህዝብ ዝናብን ሳይፈራ እያንዳንዱ ሰዉ ባንዲራ ይዞ በማዉለብለብ አዉሮፕላን ጣብያ ተቀበላት ተቀበላት፣ ከኡሮፕላን ስትወርድም ልዩ ቀይ ምንጣፍ ተዘረጋላት የኒደርዛክሰኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የላኩላትን እቅፍ አበባ አዉሮፕላን ስትወርድ አአረከቱላት በማርጨዲስ ተሳፍራ በሞተርሳይክል ታጅባ በኒደርዛክሰን ጠቅላይ ግዛት ዋናከተማ ሃኖቨር መዘጋጃቤት ሄዳ በወርቅማዉ የክብር ደብተር ላይ ፊርማዋን እና ማስታወሻዋን አኖረች ልዩ መንግስታትም ሲመጡ ይህን ያህል አቀባበል አልተደረገላቸዉም ከዝያም ህዝብ ወደ ሚጠብቃት ልዩ መድረክ ደረሰች፣ በመጀመርያ ታድያ ያዉ የተለመደዉን ሙዚቃ ማለት ጀርመንን እወረዳለሁ ጀርመንን እወዳለሁ የሚለዉን ሙዚቃ በጋራ ከህዝብ ጋር አዚማ አሸናፊ የሆነችበትን ሙዚቃ ከጎንዋ የቆመዉን ህዝብ መናመስገን አዜመች

Aschenputtel ሰንደሪላ የሚል ስያሜን የሰጥዋት እና በወቅቱ ሙዚቃዋ በተለያዩ የብዙሃን መገናኛዎች የሚስተጋባዉ ሌና በርግጥ የተለየ ድምጽ ኖርዋት ሳይሆን ወጣትነትዋ የደም ግባትዋ ለዛዋና መስብዋ እና ሙሉበራስ መተማመን ጸባይዋ የብዙሃኑን ልብ ማነሁለሏ እንደነበር ይነገርላታል። የዘንድሮዉ የአዉሮጻ ሙዚቃ ዉድድር አዘጋጅ ኖርዊ ኦስላ ላይ በተካሄደዉ የሙዚቃ ዉድድር ላይ ሰላሳ ዘጠኝ አገራት ለግማሽ ፍጻሜ ዉድድር ቀርበዉ እና ተወዳድዉ ሃያ አምስት አገሮች ለፍጻሜ ዉድድር ቀርበዉ ጀርመን አሸናፊ የሆነችዉ።

አንድ አገር ይዞት የሚቀርበዉ ሙዚቃ ከሶስት ደቂቃ ያልበለጠሲሆን ስርጭቱ በበርካታ አዉሮጻ እስያ እንዲሁም ሩቅ ምስራቅ አገራት በቀጥታ ስርጭት በመተላለፍ ለዉድድር የቀረቡት ባጠቃላይ ሰላሳ ዘጠኝ አገራት ስልክ በመደወልከሚኖሩበት አገር ሌላ ለቀረቡት ሃያ አራት አገራት ነጥብ በመስጠት አሸናፊዉ የሚለየዉ። ታድያ በዘንድሮዉ ዉድድር ጀርመናዊትዋ አሸናፊ 246 ነጥብ በማግኘት አንደኛ በመሆን እስከዛሪ ከተደረጉት ዉድድች ከፍተኛ ቁጥር በማምጣት የመጀመርያዋ ስትሆን በሁለተኝነት የቱርኩ ተወዳዳሪ መዚቀኛ 170 በማምጣት ሁለተኛ እንዲሁም ሮማኒያዊትዋ 162 ነጥብን በማግኘት የሶስተኝነትን ቦታ አግኝታለች።

Eurovision Song contest የተሰኘዉ የሙዚቃ ዉድድር አዉሮጻዉያን እርስ በርስ ጦርነትን አቁመዉ ለጋራ መተሳሰር እና መግባባት እና በመደጋገፍ የጀመሩት ያጋራ መድረክ ሲሆን ሁለተኛ አለም ጦርነት በተጠናቀቀ በአስራ ሁለተኛ አመቱ እንደ አዉሮጻዉያን አቆጣጠር 1956 የአዉሮጻ የራድዮ ስርጭት ማህበር ለመጀመርያ ግዜ ያቋቋመዉ የሙዚቃ ዉድድር እንደሆነም ጽሁፎች ይጠቁማሉ። ነገሩ አዉሮጻዉያን ተሰኘ እንጂ የራድዮ ማህበር አባል አገርራት ሁሉ የሚሳተፉበት ሲሆን የማህበሩ አባላት እስራኤልን የእስያ አገራትን እንዲሁም የሰሜን አፍሪቃ አገራትንም ያጠቃልል። እስከዛሪ በዚህ ዉድድር ከአፍሪቃ ሞሮኮ እንደ አ.አ 1980 አ.ም የተሳተፈች ሲሆን ከአዉሮጻዉ የራድዩ ስርጭት ማህበር በዚህ የሚቃ ዉድድር እስከዛሪ ያልተሳተፉ አገራት አልጀርያ ቱኒዚያ ሊቢያ ግብጽ ዮርዳኖስ እና ሊባኖን ይገኙበታል። የአዉሮጻ የራድዩ ስርጭት ባህበር አባላት ባጠቃላይ ሰባ አምስት ሲሆኑ ሃምሳ ስድሱ አዉሮጻ ዉስጥ የሚገኙ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ ሰሜን አፍሪቃ እና እስያ ዉስጥ የሚገኙ አገሮች ናቸዉ። ዘንድሮ ለ 55ኛ ግዜ የተደረገዉ የአዉሮጻዉ የሙዚቃ ዉድድር አዘጋጅ የሆነችዉ ኖርዊ ባለፈዉ የአዉሮጻዉያኑ አመት የተዘጋጀዉን ዉድድር አሸናፊ በመሆንዋ ነበር።

አሁንም በመቀጠል ጀርመን የዚህን የሙዚቃ ዉድድር አዘጋጅ በመሆንዋ ዝግጅቱን ዉጤቱን ከሰማችበት ቀን ጀምሮ ዝግጅቱን ቀጥላለች።

በዚህ የዉድድር መድረክ አሸናፊዎች ወደ ሰማንያሽህ ይሮ እንደሚያገኙ ሲገለጽ በሌላ በኩል የተለያዩ የአዉሮጻ አገራት የተለያዩ ስራዎች እና የራድዮ ቃለ መጠይ በማድረግ እንዲሁም ራስን በማስተዋወቅ የሙዚቃ ስራቸዉን በመሸጥ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያገኙ ተገልጾአል።

እ.አ 1965 አ.ም ለመጀመርያ ግዜ በኦስትርያ ሉጋኖ ዉስጥ የተካሄደዉ ይህ የአዉሮጻ የሙዚቃ ዉድድር መድረክ በአለም ዙርያ ተወዳጅ የሆኑ ሙዚቀኞችን አፍርቶአል። ለምሳሌ በአለም ታዋቂዋ የፖፕ የሙዚቃ ተጫዋች ሴሊን ዲዮን የአዉሮጻዉ የዉድድር መድረክ ለሰላሶስተኛ ግዜ ባቀረበዉ የዉድድር መድረክ ላይ ተሳትፍ ባቀረበችዉ የፈረንሳይኛ ሙዚቃ ነዉ። የአለም የሙዚቃ መድረክ ኮከብ ለመሆን የበቃችዉ።

ABBA በመባል የታወቀው የስዊድን የፖፕ ሙዚቃ ባንድ አባላትም፤ እ ጎ አ በ1974 ዓ.ም፤ waterloo የተሰኘዉን ሙዚቃ አቅርበዉ በማሸነፍ በአለም ተደናቂነትን አግኝተዋል።

Die schwedische Popgruppe ABBA
ABBA በመባል የታወቀው የስዊድን የፖፕ ሙዚቃ ባንድምስል AP

ጀርመናዉያን ባንዲራን ይዞዉ እያዜሙ በደስታ አደባባይ እዲፈነጥዙ ያደረገዉ የአዉሮጻዉያኑ የሙዚቃ ዉድድር መድረክ እና ዉጤቱ ፣ ፖለቲከኞችም ቢሆኑ ከዉድድሩ በፊት ጀርመን የዘንድሮዉን ዉድድር እንድታሸንፍ በየበኩላቸዉ ጥሩ ምኞትን ተመኝተዋል ከድሉም በኻላ ያልፈነጠዘ አንካን ደስ ያለን ያላለ አልነበረም። የፖለቲካዉም መድረክ ቅድምያ የመነጋገርያ ርእስ ሆኖ ነበር የዘለቀዉ። በጀርመን ይህን አይነት ፈንጠዝያ በኳስ ግጥምያ ረገድ ታየ እንጂ፣ በሌላ ህዝብን በነቂስ ያስወጣ ደስታ አልታየም። ታድያ የድሉ ፈንጠዝያ ገና ከመግባቱ በድንገት የጀርመኑ ርእስ ብሄር ስልጣን መልቀቃቸዉን ህዝቡ ጭፈራዉን ቆም አድርጎ ዉይ እንዲል ሳያደርገዉም አልቀረም ብቻ የወጣትዋ ጀርማናዊት ያሸናፊ ሙዚቃ በብዙሃን መገናኛዎች ጠዋት ማታ መሰማቱ ቀጥሏል። አሸናፊዋ ሌናም በተለያዩ የጀርመን የብዙሃን መገናኛዎች በመዘዋወር የኦስሎዉን ተመክሮዋን በመግለጽ ላይ ናት። የጀርመን ካቢኔም እንደ ባህሉ ለጀርመን ርእሰ ብሄር በሰላሳ ቀን ዉስጥ ለመምረጥ ንግግሩን ቀጥሎአል። የመገናኛ ብዙሃንም ሌና በአሸናፊነት ጀርመንን ማስደሰት ማስጠራት የጀመረችበት ሁኔታ፣ ወጣት የእግር ዃስ ቡድናችንም በሚቀጥለዉ ሳምንት የሚጀመረዉን የአለም የእግር ኻስ ጨዋታን ድልን ተቀዳጅተዉ መምጣታቸዉ ጥርጥር የለዉም በሚል የእግር ዃስ ቡድናቸዉን ወኔ እየሰጡ ይመስላል።

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ