1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን ግዙፍ ግንባታዎችና እንቅፋታቸዉ

ረቡዕ፣ ጥር 1 2005

ብዙውን ጊዜ ኃላፊነት የጎደለው ሥራ ብቻ ሳይሆን የወንጀል አሰራርም ሲፈጸም ይታያል። ከዚህ በፊት በኮሎኝ ከተማ አንድ ታሪካዊ ቤተ መዝገብ ፈርሶ ሁለት ሰዎች ለህልፈተ የተዳረጉት በከርሰ ምድር የተገነባው የባቡር መስመር ጥራት በጎደለው እቃ በመሰራቱ እንደነበር በምሳሌነት ይጠቀሳል።

https://p.dw.com/p/17Goj
ARCHIV - Das World Conference Center Bonn (WCCB) am Montag (15.08.2011) in Bonn. Der Prozess um das Millionendebakel beim Bau des Bonner Konferenzzentrums beginnt am 30. September. Dem Investor, dem Südkoreaner Man-Ki Kim, wirft die Anklage zwölffachen Betrug, Untreue und Bestechung vor. Angeklagt sind nach Angaben des Bonner Landgerichts vom Mittwoch (21.09.2011) zudem ein früherer städtischer Berater, ein Rechtsanwalt sowie ein als Rechtsberater aufgetretener Jurist. Bisher sind bis Ende Januar 28 Prozesstage terminiert. Foto: Oliver Berg dpa/lnw +++(c) dpa - Bildfunk+++
ያልተጠናቀቀዉ የጉባኤ ማዕከል-ቦንምስል picture alliance/dpa



አዲሱ የበርሊን አየር ማረፊያ፣ በሰሜን ጀርመን የሚገኘው የቪልሔልም የጥልቅ ባህር ወደብ ፤ የቦን ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል በጀርመን እየተካሄዱ ካሉ ትላልቅ የግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው። እኚህ ፕሮጀክቶች ከተያዘላቸው ወጪና ጊዜ አኳያ መጠናቀቅ አልቻሉም። በኢንዱስትሪ በበለጸገችው ጀርመን ውስጥ እንዲህ ያሉ የግንባታ ሥራ ቅሌቶች የጀርመን ማህበረሰብ አስቆጥተዋል። ኢንሳ ሬዴ ያቀናበረችውን ገመቹ በቀለ ያቀርበዋል።

ጀርመናውያን ሥራ ወዳድ፣ ሰዓት አክባሪና ታታሪ ሰራተኞች እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። እነሱ የጀመሩት ነገር ይሳካል ይባላል፣ ቢያንስ በዝና። ሆኖም ግን ገሀዱ ሁሌ እንደሚባለው አይደለም። በጀርመን ትላልቅ የግንባታ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ አለመጠናቀቅ፣ ከተመደበላቸው የገንዘብ ወጪ በላይ መፍጀት፣ ግድ የለሽነት፣ ማጭበርበርና የሙስና ችግርም ይታይባቸዋል። ለምሳሌ በበርሊን እየተገነባ ያለው ዋና የባቡር ጣቢያ ሲጀመር 300 ሚሊዮብ ዩሮ እንደሚያስፈልገው ነበር የታቀደው። በስተመጨረሻ ግን 1,2 ቢሊዮን ዩሮ ወጪ ተደርጎበታል። ከ12 ዓመት በፊት እአአ 2007 ያልቃል ተብሎ የታቀደው የበርሊኑ ዓለም አቀፍ አየር ማሪፊያም እስካሁን ድረስ አልተጠናቀቀም። ከዚህ በላይ በመገናኛ በዙኃን ዘገባ መሰረት፣ ፕሮጀክቱ ሲጀመር የታቀደው ወጪ በእጥፍ ጨምሮ 4,3 ቢሊዮብ ዩሮ እንደሚያወጣ ተገልጾዋል።

«በጀርመን ውስጥ እስከ ቅርብ ዓመታት ድረስ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ይሰጡ የነበረው ለግዙፍ የሥራ ተቋራጭ ድርጅቶች ነበር። ያ ማለት አንድ ድርጅት ሁሉንም፣ አስፈላጊ እቃዎችን፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮዎችን፣ ማስዋቢያ እቃዎችንና ሌሎችንም ራሱ አቅርቦ ይቆጣጠር ነበር። »

ይላሉ ድሪስ ና ሶመር በተሰኘው የህንጻ ግንባታ አማካሪ ድርጅት ሊቀመምበር የሆኑ ፒተር ትሴሽሎክ። እንዲህ አይነቱ አሰራር ግን ድርጅቶቹ እጅግ ከፍ ያለ ተጨማሪ ወጪ ስለሚጠይቁ በጣም ውድ ነው። ስለዚህ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ለብዙ ጥቃቅን ድርጅቶች መሰጠት ተጀመረ። ጥቃቅኖቹ ድርጅቶች አንዳንዴ እስከ መቶ ሊደርሱ ይችላሉ። በዚህም ምክንያት የሥራ አስተባባሪዎች በተለያዩ ድርጅቶች የሚከናወኑ የተለያዩ ሥራዎችን መቆጣጠሩ ፈተና ሆኖባቸዋል ይላሉ ሚስተር ፒተር ትሴሽሎክ፣

«የሥራ ተቋራጩ ባለቤት ሁሉንም መቆጣጠር ሲችል ከ20 እስከ 30 በመቶ የሚደርስ አላስፈላጊ ወጪን የመቀነስ እድል አለው። ይህ በመቶ ሚሊዮን ዩሮ ለሚከናወኑ የፕሮጀክት ሥራዎች በርግጥ ግዙፍ የገንዘብ መጠን ነው። ችግሩ ያለው ግን ድርጅቱ የበለጠ ኃላፊነት መሸከሙ ጋ ነው። የወጪና ጊዜ እንከን ያጋጠማቸው ሁሉም ትላልቅ ፕሮጀክቶች የተለያዩ ጥቃቅን ሥራዎች በደንብ ያለመቀናጀት ድክመት ይታይባቸዋል። »»

ከዚህም የቅንጅት ችግር በተጓዳኝ ፕሮጀክቶችን ለመስራት ኃላፊነት የወሰዱ ባለሙያዎች መለዋወጥም ሌላው ችግር ነው። አሰሪዎቹ በተለወዋጡ መጠን የሚወጣው ወጪም እንዲው ይጨምራል። ይህ መለዋዋጥ የወጪ መጨመርን ጨምሮ ሌሎች ችግሮችንም ይዞ ይመጣል ባይ ናቸው ሚስተር ፒተር ትሴሽሎክ፤

«የወጪ መጨመር የተያዘው የጊዜ ገደብ መራዘምን ፣ ማለትም፣ ከታቀደው ጊዜ በላይ መስራትን ያስከትላል። ለዛ ነው አሰሪዎቹ መጀመሪያ በያዙት ጊዜ ውስጥ ሥራውን ለመፈጸም የሚቻኮሉት። በዚህም ጊዜ ኃላፊነት የጎደለው ሥራ ይሰራል። ተቋማት በተያዘላቸው የገደብ ውስጥ ለመጨረስ ስለሚጣደፉ፣ የሥራው ጥራት ይወድቃል።»

ብዙውን ጊዜ ኃላፊነት የጎደለው ሥራ ብቻ ሳይሆን የወንጀል አሰራርም ሲፈጸም ይታያል። ከዚህ በፊት በኮሎኝ ከተማ አንድ ታሪካዊ ቤተ መዝገብ ፈርሶ ሁለት ሰዎች ለህልፈተ የተዳረጉት በከርሰ ምድር የተገነባው የባቡር መስመር ጥራት በጎደለው እቃ በመሰራቱ እንደነበር በምሳሌነት ይጠቀሳል። የሥራ መጓተት፣ የወጪ መናር፣ እንዲሁም፣ የወንጀል ተግባራት ቢፈጸሙም፣ የጀርመን የህንጻ ግንባታ ዘርፍ በውጪው ዓለም ዛሬም መልካም ስም አለው ይላሉ ፒተር ትሴሽሎክ፤

«የጀርመን የኢንጂነሪን እውቀት ፣ የጀርመን እሴቶች፣ አስተማማኝነትና ግልጽነት፣ እኚህ ናቸው የኛ ዓለም አቀፍ የንግድ ድርጅቶች የሚታወቁበት ሥሞች። ይህ በጀርመን ሀገር የሚነገረው ሙስና ድርጅቶቻንን በተመለከተ በውጪው ዓለምም አይሰማም ስለዚህም ዬትም አይነገርም። አሁን በውጭ ሀገራት በብዙ ቦታ እንገኛለን።»

Die Lampen im Terminal des neuen Flughafens Berlin Brandenburg Willy Brandt (BER) in Schönefeld (Brandenburg) bei Berlin leuchten am 07.01.2013. Für den Hauptstadtflughafen Berlin Brandenburg muss ein neuer Eröffnungstermin gesucht werden. Die für den 27. Oktober geplante Inbetriebnahme ist vom Tisch, wie am 06.01.2013 bekanntwurde. Mehrere zuverlässige Quellen bestätigten der Nachrichtenagentur dpa die unvermeidliche Absage. Foto: Bernd Settnik/dpa
በርሊንምስል picture-alliance/dpa
Blick aus einem Kleinflugzeug am 04.09.2012 auf den neuen Flughafen Berlin Brandenburg Airport Willy Brandt in Schönefeld. Brandenburgs Landesregierung geht von einer neuerlichen Verschiebung der Flughafeneröffnung in Schönefeld aus. Der Aufsichtsrat berät am 07.09.2012 über den weiteren Terminplan. Die Eröffnung des Flughafens war vom 3. Juni 2012 auf den 17. März 2013 verschoben worden. Foto: Patrick Pleul
ጅምሩ አዉሮፕላን ማረፊያ-በርሊንምስል picture alliance/ZB

ገመቹ በቀለ

አርያም ተክሌ