1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን፤ 55ኛዉ የዓለም የፀጥታና ደህንነት ጉባዔ

ዓርብ፣ የካቲት 8 2011

ከ 40 በላይ የዓለም መንግሥትና የመንግሥታት ተጠሪዎች ታዋቂ ፖለቲከኞች የሚሳተፉበት በጀርመን ሙክ ከተማ ላይ ዛሬ በይፋ የጀመረዉ ጉባዔ በዓለማችን የሚገኙ ፖለቲከኞች ፤ የፀጥታ እና የመከላከያ ጉዳይ ምሑራን ትልቅ እዉቅና የሚሰጡት ዓለም አቀፍ ጉባዔ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3DUAA
Münchener Sicherheitskonferenz 2019
ምስል MSC

55ኛዉ የዓለም የፀጥታና ደህንነት ጉባዔ ዛሬ ምሽት ላይ በደቡብዊ  ጀርመን በባቫርያ ግዛት ሙኒክ ከተማ ጀመረ። ከ 40 በላይ የዓለም መንግሥትና የመንግሥታት ተጠሪዎች ታዋቂ ፖለቲከኞች የሚሳተፉበት ይህ ጉባዔ በዓለማችን የሚገኙ ፖለቲከኞች ፤ የፀጥታ እና የመከላከያ ጉዳይ ምሑራን ትልቅ እዉቅና የሚሰጡት ዓለም አቀፍ ጉባዔ በመሆኑ ይታወቃል። እስከ ፊታችን እሁድ ምሽት በሚዘልቀዉ የሙኒኩ የዓለም የፀጥታና ደህንት ጉባዔ ላይ የጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ተካፋይ ናቸዉ። በዘንድሮዉ ጉባዔ   በርካታ አባላት ያሉት ልዑክ የላከችዉ ቻይና ናት።

 

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ