1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀዋር መሐመድና በቀለ ገርባ በቁጥጥር ስር ናቸዉ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 23 2012

አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ በፌድራል የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ በተለይ ለዶቼ ቬለ አረጋገጠ። በሚዲያ ተቋሙ የሚያገለግለዉ ጋዜጠኛ ኡስማን ኡኩሚ እንደገለፀዉ ፤ ጋዜጠኞች ታስረዋል፤ አዲስ አበባ የሚገኘዉ የስርጭት ጣብያም ፕሮግራሙ እንዲቋረጥ ተደርጓል ብሎአል።

https://p.dw.com/p/3ebDX
Logo Oromia Media Network

 

አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ በፌድራል የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ በተለይ ለዶቼ ቬለ አረጋገጠ። በሚዲያ ተቋሙ የሚያገለግለዉ ጋዜጠኛ ኡስማን ኡኩሚ እንደገለፀዉ ፤ ጋዜጠኞች ታስረዋል፤ አዲስ አበባ የሚገኘዉ የስርጭት ጣብያም ፕሮግራሙ እንዲቋረጥ ተደርጓል ብሎአል። ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ  በሰራው ዘገባ  ጀዋርን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በተደረገው ጥረት የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ከፌድራል የጸጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር። ዘግየት ብሎ በወጣ መረጃ ተይዘዉ የነበሩት አንዳንድ ጋዜጠኞች ተለቀዋል። በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘዉ የኦሮሚያ ኔት ወርክ ጋዜጠኛን ከስርጭታችን በፊት አናግረነዉ ነበር።

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ