1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ መታሰራቸውን ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዘገበ 

ማክሰኞ፣ ሰኔ 23 2012

አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ በፌድራል የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ዘገበ።  ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ከደቂቃዎች በፊት በሰራው ዘገባ እንዳለው ጀዋርን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በተደረገው ጥረት የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ከፌድራል የጸጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር። 

https://p.dw.com/p/3ea51
Äthiopien Addis Abeba Oppositionsführer Jawar Mohammed
ምስል picture-alliance/AP Photo/M. Ayene

አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ በፌድራል የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ዘገበ።  ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ከደቂቃዎች በፊት በሰራው ዘገባ እንዳለው ጀዋርን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በተደረገው ጥረት የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ከፌድራል የጸጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር። 

በሁለቱ ኃይሎች መካከል በተፈጠረው ፍጥጫ ጉዳት ስለመድረሱ የዘገበው ኦኤምኤን ተጨማሪ ማብራሪያ ግን አልሰጠም። የፌድራል የጸጥታ አስከባሪዎች ኃይል ጨምረው የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ አመራሮችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋሉ የቴሌቭዥን ጣቢው ዘግቧል።

ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ «ለጊዜው የታሰሩበት ቦታ አልታወቀም» ብሏል። በውጭ አገር የተመሠረተው እና አቶ ጀዋር መሐመድ በኃላፊነት ሲመሩት የነበሩት ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የአዲስ አበባ ስቱዲዮ መዘጋቱ ተረጋግጧል። 

የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ የአዲስ አበባ ስቱዲዮ ሰራተኞች በፌድራል የጸጥታ አስከባሪዎች መያዛቸውን በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፁ ባሰራጨው መረጃ አስታውቆ ነበር። የቴሌቭዥን ጣቢያው ሰራተኞች የት እንደተወሰዱ እንደማይታወቅ ገልጿል። 

የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ የድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ከተሰማበት ቅፅበት ጀምሮ በተከታታይ በኩነቱ ላይ አተኩሮ ሥርጭት ሲያከናውን ቆይቷል።