ጂዳ፥ የኢትዮጵያዉያን መጠለያ መዘጋት
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 5 2005ማስታወቂያ
ጂዳ-ሳዑዲ አረቢያ የሚገኘዉ የኢትዮጵያዉያን ችግረኞች ጊዚያዊ መጠለያ ጣቢያ አገልግሎት በማቋረጡ ተፈናቃይ ኢትዮጵያዉን መቸገራቸዉን አስታወቁ።መጠለያ ጣቢያዉ ለአዳዲስ ተፈናቃዮች አገልግሎት መስጠት ያቋረጠዉ አንዳዶች እንደሚሉት በአካራዮች፥ በኢትዮጵያ ቆንስላና በኢትዮጵያ ማሕበረሰብ መካካል በተፈጠረ ዉዝግብ ነዉ።የጂዳዉ ወኪላችን ነቢዩ ሲራክ እንደዘገበዉ መጠለያ ጣቢያዉ በመዘጋቱ የአዕምሮ በሽተኞችን ጨምሮ ተፈናቃዮች እየተንገላቱ ነዉ።ዝር ዝሩ እነሆ
ነቢዩ ሲራክ
ነጋሽ መሐመድ