1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጄኮብ ዙማ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 1 2001

አዲሱ የደቡብ አፍሪቃ ምክር ቤት ባለፈው ረቡዕ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት አድርጎ የመረጣቸወ የአፍሪቃውያኑን ብሄረተኞች እንቅስቃሴ ኤ ኤን ሲ መሪ ጄኮብ ዙማ ዛሬ ቃለ መሀላ ፈጸሙ።

https://p.dw.com/p/HmO3
ምስል AP

ከ አራት መቶ የምክር ቤት እንደራሴዎች መካከል የሁለት መቶ ሰባ ሰባቱን ድምጽ ያገኙት ዙማ በነገው ዕለት ካቢኔአቸውን ይፋ ያደርጋሉ። ይህ ደቡብ አፍሪቃ ወደፊት የምትከተለውን ፖሊሲ የሚጠቁም በመሆኑ ብዙዎች በስጋት በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ዙማ በሀገሪቱ የዘር አድልዎ አመራር ከተገረሰሰ በህዋላ ለአራተኛ ጊዜ የተመረጠው ዴሞክራሲያዊ መንግስት አመራርን ነው ዛሬ የተረከቡት።

LS/AA/RTR