1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጅዳ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ት/ቤት

ሐሙስ፣ ጥር 28 2001

ከአገር ዉጪ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ትምርት ቤቶች መካከል የጅዳ ዓለም ዓቀፍ ትምህርት ቤት በአንጋፋነቱ ተጠቃሽ ነዉ።

https://p.dw.com/p/Go1P
ምስል AP

በትምህርት ቤቱ ህንፃ ላይ በደረሰዉ የመሰረት መሸሽና የመሰንጠቅ ችግር የመማር ማስተማር ሂደቱ ተቋርጦ ሰንብቶ ከ22 ቀናት በኋላ ተመልሶ መጀመሩን የሳዉዲዉ ወኪላችን ዘገባ ያመለክታል። አዲሱ ትምህርት ቤት አብዛኛዉ ኗሪ ከሚኖርበት ከከተማዉ ወጣ ያለ ቢሆንም በትምህርት ሂደቱ መስተጓጎል የተቸገሩ ወላጆች ተቀብለዉታል። ሆኖም ለዘላቂ መፍትሄዉ ወላጅ ኮሚቴን ጨምሮ የኢትዮጵያ ቆንስላ የማኅበረሰቡን አባላት ሁሉ አሰባስቦ መላ ካልፈለገለት ለ6ወራት የተያዘዉ የአዲሱ ትምህርት ቤት ዉል ሲያበቃ የመማር ማስተማርሂደቱ ዳግም ችግር ሊገጥመዉ እንደሚችል ስጋታቸዉን እየገለፁ ነዉ።