1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጊቤ 3 ግድብና የውጭ የጥናት ቡድን ዘገባ፣

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 24 2005

ከዓለም ታላላቅ ግድቦች መከከል አንዱ እንደሚሆን የሚጠበቀው የ« ጊቤ 3 » ግድብ ፣ መጠነ -ሰፊ የሰብአዊ ቀውስና የድንበር ግጭት ሊፈጥር ይችላል ሲል ፤ አንድ ጥናት ገለጠ። የኢትዮጵያ መንግሥት፤ ይህን የሚለው ዘገባ ፣ ፕሮጀክቱ እንዳይሣካ የሚፈልጉ

https://p.dw.com/p/18QxC
Goha Tsiyon-Dejen Brücke über den Nil liegt 208 Km nördlich von Adis Abeba. Copyright: DW/Azeb Tadesse Hahn
ምስል DW/Azeb Tadesse Hahn

አካላት መሠረተ-ቢስ ክስ ነው ማለቱን ፤ የዋሽንግተን ዲ ሲው ዘጋቢአችን የአበበ ፈለቀ ዘገባ ያስረዳል።ኢትዮጵያ፤ ፣ በዐባይ ወንዝ ላይ ከሚሠራው ህዳሴ ግድብ በተጨማሪ በሌሎች ወንዞች አነስተኛ ግድቦች በመሥራት ። እ ጎ አ እስከ 2035 ባጠቃላይ 40,000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት ዕቅድ እንዳላት የኃይል ምንጭ ጉዳይ ሚንስትር ዓለማየሁ ተገኑ ከ 6 ወራት ገደማ በፊት መግለጻቸው የሚታወስ ነው። በጊቤ የሚሠራው ግድብ 3 ፣ የኦሞን ወንዝ ይቀንሳል፤ በቱርካና ሃይቅ አካባቢ የሚኖሩ አርብቶ አደሮችን ኑሮ ያናጋል በማለት ተቃውሞ ከሚያሰሙት መካከል አንዱ «ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል» የተሰኘው ለነባር ህዝብ መብት እንደሚቆረቆር የሚነገርለት ድርጅት ነው።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ