1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጋሊፖሊ-900 ስደተኞቹ ከሞት ለጥቂት ዳኑ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 22 2007

የኢጣሊያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂ ጦር ቃል አቀባይ ፊሊፖ ማሪኒ እንደሚሉት ባልደረቦቻቸዉ ባይደርሱ ኖሮ ዓለም በሌላ የባሕር ላይ ጥፋት ባዘነ ነበር።አብዛኞቹ ስደተኞች የሶሪያ ዜጎች ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/1EDiD
ምስል NUNZIO GIOVE/AFP/Getty Images

የኢጣሊያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂ ጦር በአንድ መርከብ ተሳፍረዉ የነበሩ ዘጠኝ መቶ ሥደተኞችን ከሞት አፋፋ ማዳኑንን አስታወቀ።የጦሩ አዛዦች እንዳስታወቁት ስደተኞቹን አሳፍራ ወደ ኢጣሊያ ባሕር ጠረፍ ትቀዝፍ የነበረችዉ መርከብ ሞተር ድንገት «በመንከሱ» መርከቢቱ ባሕሩ ጠረፍ ከሚገኝ አለታማ ተራራ ጋር ልትጋጭ ጥቂት ኪሎሜትር ነበር የቀራት።አኩለ ሌሊት ግድም የተሳፋሪዎቹ የርዳታ ጥሪ የደረሳቸዉ የባሕር ሐይል ባልደረቦች ከሔሊኮፕተር መርከቢቱ ላይ ወርደዉ ሞተሩን አላቀዉ፤ የመርከቢቱን አቅጣጫ ማስቀየር ችለዋል።የኢጣሊያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂ ጦር ቃል አቀባይ ፊሊፖ ማሪኒ እንደሚሉት ባልደረቦቻቸዉ ባይደርሱ ኖሮ ዓለም በሌላ የባሕር ላይ ጥፋት ባዘነ ነበር።አብዛኞቹ ስደተኞች የሶሪያ ዜጎች ናቸዉ።

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ