1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጋምቢያ-ተጠርጣሪዎች እየታሰሩ ነዉ

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 25 2007
https://p.dw.com/p/1EEeY

የጋምቢያ መንግሥት ባለፈዉ ማክሰኞ መፈንቅለ መንግሥት ከሞከሩ የጦር መኮንኖች ጋር ግንኙነት አላቸዉ ብሎ የጠረጠራቸዉን የጦር መኮንኖች ማሠሩን ጥሎአል። በመፈንቅለ መንግሥት ወደ ስልጣን ከመጡ 20 ዓመታቸዉን የያዙት ፕሬዝዳንት ያሕያ ጃሜሕ ሴራዉን የዶለቱት ዩናይትድ ስቴትስ፤ ጀርመንና ብሪታንያ የሚኖሩ ናቸዉ በማለት አዉግዘዋል። እንዲሁም የኬንያ መንግሥት ከሁለት ሳምንት በፊት ያፀደቀዉ የፀረ-ሽብር ሕግ አንዳድ አንቀፆች ተግባራዊ እንዳይሆኑ የሃገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትናንት ማገዱ ይታወቃል። የኬንያ ፀረ ሽብር ሕግና የፍርድ ቤቱ ርምጃ የዕለቱ ትኩረት በአፍሪቃ መሰናዶ የመጀመርያዉ ርዕስ ነዉ። የዕለቱ ትኩረት በአፍሪቃ ሁለተት ርዕሶችን ይዞአል።