1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጋውክ፤ «ጀርመን ልትደበቅ አይገባትም»

እሑድ፣ የካቲት 16 2006

«ጀርመን ያለባትን ኃላፊነት ልትወጣ ይገባል» ሲሉ የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ዮሀይም ጋውክ አስታዉቀዋል። ባለፈው ዓርብ የዶይቸ ቬለ የቴሌቪዥን ጣብያ ክፍል ኃላፊ ዳግማር ኤንግል ከፕሬዚዳንቱ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገዋል።

https://p.dw.com/p/1BE8M
Gauck DW Interview 21.02.2014
ምስል Bundespresseamt/Jesco Denzel

ቀደም ሲል የወላጆቻቸው ትውልድ በፈፀመው የዘር ጭፍጨፋ ጋውክ እራሳቸውን እንደ ጀርመናዊ መቁጠር ሁሉ ይከብዳቸው እንደነበር ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ እንደሚሉት ሀገራቸዉ ባለፉት አስርተ ዓመታት ከፍተኛ መሻሻል አድርጋለች «በአሁኑ ወቅት ጀርመን በጦርነቱ ጊዜ ከነበረው ፍፁም የተለየች ነች» ሲሉ ስለ ሀገራቸው ገልፀዋል። ዛሬ ጀርመን ከሌሎች የአውሮጳ ሀገራት ጋር ስትነፃፀር፤ ሀገራቸው ዲሞክራሲ የሰፈነባት ለመሆኗ ምንም አይጠራጠሩም። ሰላም የሰፈነባት እና በማህበረሰብ ዘንድ መቻቻል የሚታይባት ሀገርም ናት። ስለሆነም ነው ጀርመን በዓለም አቀፍ ደረጃ፤ ዴሞክራሲ የሰፈነባት ሀገር በመባል እንደ አርዓያ ለመቆር የበቃችዉ ሲሉ ጋዉክ ተናግረዋል።

የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ዮሀይም ጋውክ ለዶይቸ ቬለ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ ነገ በዜና መፅሄት ጥንቅራችን ይዘን እንቀርባለን።

ልደት አበበ
አዜብ ታደሰ