1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግልፅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምሁራን

ሐሙስ፣ መጋቢት 19 2011

በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ከ40 የሚበልጡ ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካውያን ታዋቂ ሰዎች እና ምሁራን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከአንድ ቀን በፊት ግልፅ ደብዳቤ ላኩ። DW ዶቼቬለ የደብዳቤውን ይዘት አስመልክቶ ከምሁራን አስተባባሪዎቹ አንዱ የሆኑትን ስለይዘቱ ማብራሪያ ጠይቋል።

https://p.dw.com/p/3Fpnh
Vorbereitungen Premierminister Abiy Ahmed in Frankfurt
ምስል DW/E. Fekade

«የዜግነት መብት መከበር አለበት እያሉ የሚናገሩ ስለሆኑ ስለተማመንባቸው ነው»

ደብዳቤውን ከጻፉት አስተባባሪዎች አንዱ ፕሮፌሰር አክሎግ ቢራራ ግልፅ ደብዳቤ ከዚህ በፊት ቢጻፍም ዋጋ ይሰጠዋል የሚል እምነት እንዳልነበረ አሁን ግን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የላኩበት ዋናው ምክንያት «ግልፅ ነኝ፣ ሰብዓዊ መብቶች መከበር አለባቸው ፤ የዜግነት መብት መከበር አለበት እያሉ የሚናገሩ ስለሆኑ ስለተማመንባቸው ነው፤ በቃል የሚናገሩትን በተግባር ያሳዩን» ብለዋል። ዶክተር አክሎግን ስለይዘቱ ያነጋገራቸው የዋሽንግተኑ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ተከታዩን አጠናቅሯል። 

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ