1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግሪክ ፣ የአውሮፓ ህብረትና ጀርመን

ሰኞ፣ ሰኔ 11 2004

ትናንት በተካሄደው የግሪክ ምርጫ የአውሮፓ ህብረት የቁጠባ መርህ ደጋፊ የሆነው አዲስ ዲሞክራሲ የተሰኘው የግሪክ መሃል ቀኝ ፓርቲ ማሸነፉ ለዩሮ ተጠቃሚ ሃገሮችና ለሌሎችም ትላልቅ ኤኮኖሚ ለሚያንቀሳቅሱ ሃገራት እፎይታን አስገኝቷል

https://p.dw.com/p/15HPm
ምስል AP


ትናንት በተካሄደው የግሪክ ምርጫ የአውሮፓ ህብረት የቁጠባ መርህ ደጋፊ የሆነው አዲስ ዲሞክራሲ የተሰኘው የግሪክ መሃል ቀኝ ፓርቲ ማሸነፉ ለዩሮ ተጠቃሚ ሃገሮችና ለሌሎችም ትላልቅ ኤኮኖሚ ለሚያንቀሳቅሱ ሃገራት እፎይታን አስገኝቷል ። በትናንቱ ምርጫ አዲስ ዲሞክራሲ 30 ከመቶ የመራጭ ድምፅ በማግኘት ከግሪክ 300 የፓርላማ መቀመጫዎች 129 ውን አሸንፏል ። የግራው ሲሪዛ ደገሞ 27 ከመቶ ድምፅ በማሸነፍ 71 መቀመጫ አግኝቶ 2ተኛ ደረጃን አግኝቷል ። ስለግሪክ ምርጫ ውጤትና ና ስለ አውሮፓ ህብረት አስተያየት ገበያው ንጉሴ ዘገባ አለው የጀርመን መንግሥት ግሪክ የቁጠባ ና የበጀት ማስተካከያ እርምጃዎችን ለመውሰድ ከዚህ ቀደም የገባችውን ቃል እንድታከብር ዳግም አሳስቧል ። የጀርመን ተቃዋሚፓርቲዎች ደግሞ ግሪኮችን በቁጠባ አናስጨንቅ እያለ ነው ። ስለግሪክ ምርጫ ውጤትና ና ስለ አውሮፓ ህብረት አስተያየት ገበያው ንጉሴ ዘገባ አለው የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለሚካኤል ደግሞ የጀርመኖች አስተያየት አሰባስቧል ።

Parlamentswahl Griechenland
ምስል Reuters

ገበያው ንጉሴ

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ