1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግብጽና አከራካሪው የሙርሢ አዋጅ

እሑድ፣ ኅዳር 30 2005

የግብጹ ፕሬዚደንት ሞሐመድ ሙርሢ በአገሪቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተስፋፋው የሕዝብ ተቃውሞና ዓመጽ በመገፋት ሥልጣናቸውን በማስፋት ያደረጉትን አዋጅ መልሰው ሳቡ።

https://p.dw.com/p/16yso
ምስል Reuters

ሙርሢ ካይሮ ላይ ከተለያዩ የፖለቲካ መሪዎች ጋር ከተነጋገሩ በኋላ አዋጁ መነሣቱን በይፋ የገለጹት እስላሚስቱ ፖለቲከኛ ሤሊም-አል-አኡዋ ናቸው። ይሁንና ከግብጽ እስላም ወንድማማቾች ፓርቲ የመነጩት ሙርሢ ለፊታችን ቅዳሜ በታቀደው የአዲስ ሕገ-መንግሥት ረቂቅ ሕዝበ-ውሣኔ እንደሚጸኑ ተያይዞ ተጠቅሷል። በሰላም ኖቤል ተሸላሚው ፖለቲከኛ በሞሐመድ-ኤል-ባራዳይ ሊቀ-መንበርነት የሚመራው ግራ አዘንባይና ለዘብተኛ ፓርቲዎችን ያሰባሰበ ተቃዋሚ ብሄራዊ የፈውስ ግንባር በዛሬው ዕለት ተሰብስቦ በቀጣይ ዕርምጃው ላይ እንደሚነጋገር እየተጠበቀ ነው። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ጋማል አይድ በበኩላቸው የሙርሢ አዋጅ መሳብ ታክቲካዊ መሆኑን ጠቅሰው በሕገ-መንግሥቱ ረቂቅ ውስጥ የእስላም ሕግ መካተቱቱን እንደማይለውጠው አስገንዝበዋል። ይህ በእንዲህ እንለ ፕሪዚደንት ሞሐመድ ሙርሢ አክራሪ የሕገ-መንግስት ረቂቃቸዉን ለሕዝብ ዉሳኔ ለማቅረብ የሚያደርጉት ግፊት የቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ እንደቀጠለ ነዉ። የአገሪቱ ጦር ሃይል በበኩሉ ሁሉም ወዝግብ የሚመለከታቸዉ ወገኖች ችግሩን በንግግር እንዲፈቱ ጥሪ አድርጎአል።

አዜብ ታደሰ

መስፍን መኮንን