1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግብፅ ከአብዮቱ ማግስት

ሰኞ፣ የካቲት 7 2003

ግብፅ ለሶስት አስርት ዓመታት ከገዟት ፕሬዝደንት ሙባረክ የስልጣን ዘመን ማክተም በኋላ መንታ መንገድ ላይ ቆማለች።

https://p.dw.com/p/R0lJ
ደሞዝና ሥራ ጠያቂዎች በካይሮምስል AP

በአገሪቱ የሙባረክ አገዛዝ እንዲያከትም ያስገደደዉ የህዝብ አመፅ፤ እሳቸዉን ከመንበራቸዉ አዉርዶ ቢዘናቀቅም፤ ተቃዉሞዉን የቀሰቀሰዉ አብይ ጉዳይ ገና ምላሽ እንዳላገኘ ተቃዋሚዎች እየገለፁ ነዉ። ባንክን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ሠራተኞች ሙስናን በመቃወምና የደሞዝ ጭማሪ በመጠየቅ የስራ ማቆም አድማ መትተዋል። ህዝቡ እንደጨካኝ ሲመለከተዉ የቆየዉ የአገሪቱ ፖሊስ አባላትም እነሱም በሙባረክ ስርዓት ተጎጂዎች ነን በሚል ከህዝብ ጎን መቆማችን እንዲታወቅ ሲሉ ትናንትናና ዛሬም ሰልፍ ወጥተዋል። በትረ ስልጣኑን የጨበጠዉ የወታደራዊ ኮሚሽን በበኩሉ፤ ህዝቡ ወደስራዉ እንዲመለስ በመጠየቅ በስድስት ወራት ጊዜ ዉስጥ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በግብፅ እንዲካሄድ አደርጋለሁ ብሏል።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ