1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ግጥም በመሰንቆ» በጎንደር

ሐሙስ፣ ሐምሌ 30 2007
https://p.dw.com/p/1GB8L


«ግጥም በመሰንቆ በጣም ጥሩ ዝግጅት ነዉ አንደኛ ወጣቱ ያለዉን የሥነ-ጽሑፍ ክህሎት እንዲበረታታ፤ በሌላ በኩል ክህሎቱን ለማኅበረሰቡ እንዲያቀርብ፤ እንዲሁም ልምዱን እንዲለዋወጥ የሚያስችለዉ አይነት አዘገጃጀት ነዉ ያለዉ» በጎንደር ከተማ ነዋሪ የሆኑት መምህር ጎይቶም ኃይሌ የሰጡ አስተያየት ነዉ።
ጎንደር ከተማ ላይ የተጀመረዉ «ግጥም በመሰንቆ» የሥነ-ግጥም ምሽት ወጣት አዋቂዉን በሥነ -ጽሑፍ ገበታ እያሰባሰበ እንደሆነ ተነግሮለታል። ከዚህ ሌላ ከተማይቱ ከሌሎች ከተሞች ይህንኑ የሥነ-ግጥም መድረክ ለመካፈል በሚመጡ ፀሐፍትና የሥነ-ግጥም አድናቂዎች እየተጎበኘች ነዉ። የዚህ ዝግጅት አስተናባሪዎች እንደሚሉት ግጥም በመሰንቆ ዝግጅት የጎንደር ከተማን እሴት ባህልና ወግ ታሪካዊ ዳራዋን ሳይለቅ ለመዘከር፤ ከትዉልድ ትዉልድ ለመቀባበል ነዉ። በዕለቱ ዝግጅታችን በጎንደር ከተማ በወሩ የሚዘጋጀዉን የሥነ-ግጥም ገበታን እንቃኛለን።