1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግጭትና ቀውስ ለጤና ዘርፍ ጫና ማሳደሩ

ረቡዕ፣ ግንቦት 7 2011

ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰቱ ቀውስ እና ግጭቶች በጤናው ዘርፍ ሥራ ላይ ከባድ ተፅዕኖ ማስከተላቸውን የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ተቋም አመለከተ።

https://p.dw.com/p/3IYWZ
Äthiopien Vertriebene
ምስል Tizalegn Tesfaye

ግጭትና ቀውስ ለጤና ዘርፍ ጫና ማሳደሩ

 በተለይም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የሚኖሩ ዜጎችን የመተንፈሻ አካላት፣ የዓይን፣ እከክ፣ ተቅማጥ እንዲሁም የሆድ ትላትል እና የሳንባ ምች በሽታዎች እያጠቋቸው መደበኛው የጤና ጥበቃ አገልግሎት ላይ ጫና እንዳሳደረበት ተቋሙ ገልጿል። በቀጣይም ንፁሕ የመጠጥ ውኃ እጥረት፣  የጎርፍ አደጋ እና የወባ ወረርሽኝ ተፈናቃይ ወገኖች ዋነኛ ስጋቶች ሆነውም መለየታቸውን አስታውቋል። ከአዲስ አበባ ሰሎሞን ሙጬ ዘገባ አለው።

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ