1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግጭት ከበኒኒሻንጉል ወደ አማራ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 24 2011

የበኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ግጭቶችን ለማስወገድ ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር እየሠራን ነው ብሏል። ባለፈው ሳምንት ቤንሻንጉል ክልል ውስጥ የተቀሰቀሰው ግጭትም ወደ አማራ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች መዛመቱን ገልጧል።

https://p.dw.com/p/3HpM6
Asosa, West-Äthiopien und Hauptstadt der Region Benishangul-Gumuz
ምስል privat

ከቤንሻንጉል ወደ አማራ ክልል የተዛመተው ግጭት

ባሕርዳር የክልሉን እና የፌዴራሉን መንግስት በሚቃወሙ ሰልፈኞች ጎዳናዋ ሲሞላ፤ የበኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ግጭቶችን ለማስወገድ ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር እየሠራን ነው ብሏል። ባለፈው ሳምንት በኒሻንጉል ክልል ውስጥ የተቀሰቀሰው ግጭትም ወደ አማራ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች መዛመቱን ገልጧል። በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ መንግሥት ቢገልጥም፤ በግጭቱ ምን ያኽል ሰው ሕይወቱን እንዳጣ ግን አልተናገረም።  

ነጋሳ ደሳለኝ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ