1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጎጂ ልምድን ለማስወገድ የተካሄደ ዘመቻ

ማክሰኞ፣ መስከረም 11 2008

በተመድ በጽሑፍ ባወጣዉ ዝርዝር መግለጫ መሰረት የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ወደ 90 ሚሊዮን ይጠጋል። ከዚህ ሕዝብ መካከል ደግሞ 52 % የሚሆነዉ ነዋሪ ከ 18 ዓመት እድሜ ክልል በታች መሆኑን የተመ የሕፃናት መርጃ ድርጅት «UNICEF» በጽሑፍ ባወጣዉ መግለጫ አትቶአል።

https://p.dw.com/p/1GaZt
Tödliche Kinderarbeit in Nigeria Erschreckende Realität
ምስል DW/A. Kriesch

[No title]

90 % ነዋሪ ሕዝብ ይፋዊ በሆነ መልኩ የትዉልድ መዝገብ የማያዉቀዉመሆኑ ነዉ የተመለከተዉ። ድርጅቱ የሕጻናትንና የልጃገረዶችን ሁለንተናዊ ጥቃትና ከጎጅ ልምድ ለመታደግ «UNICEF» በተለይ ይህ ድርጊት ጎልቶ በሚታይበት በጎንደር ከተማ ዓዉደ ርዕዮችን በመዘርጋት፤ ታላቁን ሩጫን ጨምሮ የተለያዩ ዝግጅቶችን በማካሄድ የትምርትና የንቃት ዘመቻ አካሂድዋል። ዝግጅቱ ላይ የተገኘዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አዜብ ታደሰ