1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚወስዷቸው ርምጃዎች አንድምታ

እሑድ፣ ግንቦት 19 2010

አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሀገሪቱ አንዣቧል የሚባለውን የአደጋ ስጋት ለመቀነስ የሚያደርጉትን ጥረት ቀጥለዋል። በተለያዩ አካባቢዎች በሚያደርጉት ጉብኝትም ኅብረተሰቡን በማነጋገር ሃሳብ ጥያቄዎቹን እያደመጡ ነው። በጎረቤት ሃገራት እስር ቤቶች የሚገኙ ዜጎችንም የማስፈታት ጥረት ይዘዋል።

https://p.dw.com/p/2yKzq
Äthiopien Neuer Ministerpräsident Abiy Ahmed Ali vereidigt
ምስል picture-alliance/dpa/AP/M. Ayene

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ርምጃና አንድምታው

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መግባባት እንዲሰፍንባት በሚሞክሩባት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር በምትገኘው ሀገር አሁንም የሰዎች መፈናቀል፤ የሕይወት መጥፋት እና ጉዳት ዜና እንደሆነ ቀጥሏል። አዲስ ራዕይ ይዘው መነሳታቸውን የሚገልፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ጥረት የሚያበረታታ መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል።

ግን ደግሞ ራዕይ ጥረታቸው እንዲሳካ የገለልተኛ ተቋማት ነገር ቅድሚያ ቢሰጠዉ ያሳስባሉ። ባለፉት ሳምንታት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያከናወኗቸው እንቅስቃሴዎችና ርምጃዎች ተስፋ ሰጪዎች ቢሆኑም አዲስ ራዕይ እና አስተሳሰብ ያሉትን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ግን ፈተናዎች ሊደቀኑ እንደሚችሉ ግምት የሚሰነዝሩም አልጠፉም። ዶይቼ ቬለ በዚህ ሳምንት በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚወሰዱ ርምጃዎች አንድምታ ላይ ውይይት አካሂዷል።

ሙሉውን ውይይት ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ