1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠብመንጃ በየጓዳው

ሐሙስ፣ መጋቢት 10 2001

ባለፈው ረቡዕ በደቡባዊቷ የጀርመን ንዑስ ከተማ በቪነንደን አንድ ወጣት በፈፀመው የጅምላ ግድያ ሰበብ በመላ ጀርመን የግለሰቦች የጦር መሳሪያ ባለቤትነት እና አያያዝ ህግየመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል ።

https://p.dw.com/p/HFmZ
ምስል AP

የአስራ ሰባት ዓመቱ ወጣት በአባቱ ጠመንጃ የአስራ አምስት ሰዎችንና የራሱን ህይወት ካጠፋ ወዲህ መሰል አሰቃቂ ግድያዎችን መከላከያው መንገድ ምን መሆን አለበት የሚለው ጥያቄ ከየአቅጣጫው እየተሰነዘረ ነው ። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ከሚመለከታቸው ነጥቦች ውስጥ ቀዳሚው ነው ። ከአውሮፓ መንግስታት አንዳንዶቹ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በስደተኞች አያያዝ እየተተቹ ነው ። ከነዚህም ውስጥ የፈረንሳይ መንግስት ሲገኝበት በተለይ ካሌ በተባለው የሰሜናዊ ፈረንሳይ የወደብ ከተማ የስደተኞች ሁኔታ ይበልጡን ይወቀሳል ። በዚህች ከተማ በኩል ወደ ብሪታኒያ የገቡ ስደተኞች እንደሚናገሩት የወደብ ከተማዋ ካሌ የስደተኞች የቁም ስቃይ መቁጠሪያ ስፍራ ናት ። ካሌን አልፈው ብሪታኒያ የገቡ ያሳለፉትን መከራ እንዲሁም በብሪታኒያ የስደተኞች ይዞታን የሚያስቃኝ ዝግጅትም አለን ።

DW,Spiegel online ,AFP ,DPA

ሒሩት መለሠ

ሸዋዬ ለገሠ