ጠ/ሚ አቢይና ተቃዋሚዎች፤ ኦዴፓ እና ኦዴግ ዉህደት

አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
08:46 ደቂቃ
30.11.2018

በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የተሰጡ አስተያየቶች

የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር እና የሐገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከ 70 በላይ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች እና ተወካዮች፤ በመጪዉ ዓመት ሊቀደረግ ሥለታቀደዉ ምርጫ የመጀመርያ ዉይይትን ማካሄዳቸዉ፤  ሁለቱ የኦሮሞ ፓርቲዎች፣ ኦዴፓ እና ኦዴግ፣ለመዋሃድ የሚያስችላቸውን ስምምነት አዲስ አበባ ላይ መፈራረማቸዉ

የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር እና የሐገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከ 70 በላይ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች እና ተወካዮች፤ በመጪዉ ዓመት ሊቀደረግ ሥለታቀደዉ ምርጫ የመጀመርያ ዉይይትን ማካሄዳቸዉ፤  ሁለቱ የኦሮሞ ፓርቲዎች፣ ኦዴፓ እና ኦዴግ፣ለመዋሃድ የሚያስችላቸውን ስምምነት አዲስ አበባ ላይ መፈራረማቸዉ፤ እንዲሁም የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) ከፍተኛ አመራሮች ቅዳሜ ኢትዮጵያ ይገባሉ መባሉ ሰሞኑን የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ ተጠቃሚዎች በብዛት አስተያየት የሰጡባቸዉ ርዕሰ ጉዳዮች ናቸዉ ።

የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር እና የሐገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እእንዲሁም ወደ 70 የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች በመጪዉ ዓመት ሊደረግ  ስለታቀደዉ ምርጫ ተወያይተዋል። ሮይተርስ በእለቱ ይፋ ባደረገዉ ዘገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከ 81 የተቀናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ተወካዮች ጋር መወያየታቸዉን ነዉ የዘገበዉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመክፈቻ ንግግራቸዉ እንዳሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቀራርበዉ አነስተኛ ቁጥር ያላቸዉ ጠንካራ ፓርቲዎችን መፍጠር ቢችሉ እንደሚጠቅማቸዉ መክረዋል። የዉይይቱ  ዓላማም በመጪዉ ዓመት የሚደረገዉ ምርጫ ነፃ እና ፍትሐዊ የሚሆንበትን ሥልት መቀየስ ነዉ ተብሎአል። በዚህም የዉይይቱ ሒደት ፣ የመክፈቻ፣ዋና ዋና የምርጫ ሥራዎች እና የድሕረ-ምርጫ ሥራዎች በሚባሉ ሦስት ደረጃዎች የተከፈለ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልፀዋል። ዉይይቱን ተከትሎ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በጋራ መደራጀትን በተመለከተ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከተሰጡ አስተያየቶች መካከል፤ 

ራቢ ሮባ ጃርሶ ዋቆ የተባሉ የ«DW» ተከታታይ ወይ ተባበሩ አሊያም ተሰባበሩ " ካልን ሩብ ምእተ ዓመት አስቆጠርን እኮ ኮ! ?ይላሉ።

ነጋሲ ባራኪ የተባሉ የማኅበራዊ መገናኛ ተጠቃሚ ይሄ ዛሬ የተባለ ሳይሆን በፊተም ሲባል የነበረ ነው። በጆሮአቸው ላጲስ ገብቶ እንደሆን እንጂ ለዲሞክራሲ መጎልበት የተቀናጀ አንድ ሁለት ተቀዋሚ ፓርቲ መኖር ጠቃሚ ነው። አስታውሳለው የቀድሞው ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ይህን ይመክሩ እንደነበር አስረግጬ መናገር እችላለው።  መለያየት የተቃዋሚ ቁጥርን ማብዛት ግን የገዢዉ ፓርቲ የተንኮል ስራ ነው።» ብለዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የፓርቲዎች ውህደትን በተመለከተም 70 ሆኖ ከመቅረብ ይልቅ 3 እና 4 ሆኖ መቅረብ የበለጠ እንደሚያጠናክር፥ ፓርቲዎቹ አንድ ላይ ባይሆኑ እንኳ ግንባር ቢፈጥሩ መልካም መሆኑን  መግለፃቸዉን ተከትሎ ፤ ይመስላል ፤ እሸቱ ሆሞ ኬኖ፤ በአስቀመጡት አስተያየት: ኢህአዴግ ራሱ ወደአንድ አገራዊ ፓርቲ መጠቃለል አቅቶት እየተንገታገተ 81 ፓርቲዎች ወደ3 እና 4 ፓርቲ ተጠቃለሉ ማለት ከባድ ነው። ሲሉ በዛ አድርገዉ በቃል አጋኖ ምልክት አስተያየታቸዉን ደምድመዋል።

ስለተቃዋሚ አልያም በአሁኑ መጠርያቸዉ ስለተፎካካሪ ፓርቲዎች ያላቸዉን ስጋት የሚገልፁትየ«DW» ተከታታይ ደግሞ ዳንኤል አሰፋ ይባላሉ እንደ አቶ ዳንኤል ከቲም ለማ እና ዐቢይ ጋር ፣ አሁን ባላቸው አቋምና ብቃት ጋር አብሮ ለመሄድ እጅግ … ያጠራጥራል። ፈጥነው ተዋህደው ጠንካራ ፓርቲ ካልመሠረቱ፣ ቀላል አይሆንም።» ባይ ናቸዉ።

የሺወርቅ መኮንን የተባሉ ሌላዉ የማኅበራዊ ሚዲያ ተከታታይ እና የ«DW» ደንበኛ የተቃዋሚ ፓርቲና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ዉይይት ከተከታተሉ በኋላ ያስቀመጡት አስተያየት በብዙዎች የማኅበራዊ ሚዲያ ተከታታዮች ተወዶላቸዋል።

 « ኢትዮጵያ አገራችን በአሁኑ ስአት፣ሰላም ያስፈልጋታል።ሁላችንም ለሃገራችን ሰላምና አንድነት ከዶ/ር አብይ አህመድ፣ጎን መቆም አለብን።የአገራችን ሰላም ከተረጋጋ በኃላ ምርጫ ቢደረግ ጥሩ ነው። »

ስለተፎካካሪ ፓርቲዎች ቀቢሰ - ተስፋቸዉን የገለፁት ጆሲ ጆሲ የተባሉ የ«DW» ተከታታይ በበኩላቸዉ ከጥቂቶቹ በቀር ምንም እኮ የረባ ተቃዋሚ የለም ጡረታ መውጫ የገንዘብ ምንጭ አድርገውት ነው እኮ። አሜሪካ ይሄንን ያክል አህጉር ይዛ ሁለት ተፎካካሪ ፓርቲወች ብቻ ነው ያላት። እኛ ሀገር ደግሞ በግል ጉዳይ ካልተስማሙ አዲስ ፓርቲ ይመሰርታሉ። ይሄ ለሀገር አይጠቅምም ። የህዝቡን ድምጽ ከመከፋፈል በቀር፤ አሁንም አንድ እንሁንም ቢሉ እንኳን ውስጣቸው ስለማይጸዳ ካሸነፉ ወዲያው ይለያያሉ።እውነት ጠቅላይ ሚንስትሩ ይሄንን መምከራቸው ራሱ በጣም ቅን እንደሆኑ ያሳያል። ይሁን ቢቻል ኣንደሌሎቹ ሀገሮች የዘር ፓርቲ ቢከለከል አገሪቱ ሰላም ታገኛለች። መለስ ዜናዊ እና ተከታዮቻቸዉ ኢህአዴግ እንዲያሸንፍ ብቻ የፓርቲውን ብዛት ይፈልጉት ነበረ። ሰርጎ ገቦችን እያስገቡ ይለያዩዋቸዋል።ለምሳሌ አርባ ሚሊየን ህዝብ ተቃዋሚውን ቢመርጥ እና 30 ሚሊየን መንግስትን ቢመርጥ እንኳን ከተቃዋሚው ያለው አሸናፊ የህዝብ ድምጽ 81 ፓርቲ ሲካፈለው ያንስና፤  ኢህአዴግ በቀላሉ ማሸነፍ ቻለ ማለት ነው።እስከዛሬ  የነበረው ይሄዉ ነው። አሁን ይቀየራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

አሺብ ገብረስላሴ የተባሉ የ«DW» ተከታታይ በበኩላቸዉ እሲ አስቡት የወያኔን ዘመን ተሻግረን ተቃዋሚን ወደ ተፎካካሪ አመጣን ከዚህ ሁሉ አልፎ እንጀራ አብሮ ሚበላ ገበታ አብሮ የሚቀርብ ጠቅላይ ሚኒስትር አገኘን ፍቅር የሆነ! አሉ በርግጥ የጠቅላይ ሚኒስትሩንና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎቹን ስብሰባ በፎቶ ካዩ በኋላ የሰጡት አስተያየት ነዉ።

ዘብሔረ ኢትዮጵያ የተባሉ ተከታታይ ተከታዩን አስተያየት በ«DW» የFB ገፅ ላይ አኑረዉ በርካታ ይሁንታን አግኝተዋል።  

«ክቡር ጠቅላይ ሚንስቴር ለኔ 5 አመት እኛ ኢትዮጵያውያን ምንም አይነት ፓረቲና ምርጫ ሳያስፈልገን እርሶ ለሚቀጥሉት 5 አመት እንዲመሩን እንፈልጋለን፤እምቢ የማለት ምንም አይነት መብት የለዎትም።»

በውጭ ሀገር የተመሰረተው ተቃዋሚው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ከመጪው ሀገር አቀፍ ምርጫ በፊት ከኦሮሚያ ክልል ገዢ ፓርቲ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ጋር ውህደቱን እንደሚያጠናቅቅ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ በዚሁ በያዝነዉ ሳምንት ለ« DW» ገልፀዋል። አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ሌንጮ ለታ በመጪው ምርጫ እንደማይሳተፉም አስታውቀዋል።

ሁለቱ የኦሮሞ ፓርቲዎች፣ ኦዴፓ እና ኦዴግ፣ በዚሁ በሳምንት መጀመርያ ላይ አዲስ አበባ በተካሄደ ስምምነት ለመዋሃድ የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል። አቶ ሌንጮ ኦዴግን በመወከል ስምምነቱን ሲፈርሙ በኦዴፓ በኩል ደግሞ ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ለማ መገርሳ በመግባቢያ የስምምነት ሰነዱ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል። ውህደቱን አስመልክቶ አቶ ሌንጮ ሲናገሩ “በሁለቱም በኩል ኮሚቴ ተመድቧል። ወዲያውኑ ስራ ይጀምራሉ” ብለዋል። ሂደቱ ከምርጫ በፊት ለመጠናቀቁ ሱ «ምንም ጥያቄ የለውም» ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ኦዴፓ እና ኦዴግ ጥምረትን በተመለከተ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ተከታታዮች መካከል አቡበከር ሃጂ በሰጡት አስተያየት፤

የተባሉ የ«DW ፊስቡክ ተከታታይ እንዳሉት ሌንጮ ለታ የኦሮሞ ትግል መልክት(brand) ነወ። እነ ለማ ደግሞ ይህንን ተረክበው ከፍ ወዳ አለ ደረጃ ማድረስ አለባቸው። ጥብረቱ የተቀደሰ ይመስላል ። ይህን በማየቴ ታድያለሁ! ብለዋል

ነብዩ ልዑል ሙሉጌታ በበኩላቸዉ ሀገራችን ከተስተካከለች ተቋማት ከተስተካከሉ ማን ይፈልጋል? ጥሩ ነው መንግሥት ጠንክሮ ኢትዮጵያን ማስተካከል አለበት ።

አለሙ አብዲሳ የተባሉ አድማጭ በእንጊሊዘኛ ባስቀመጡት አስተያየት ደግሞ በአሁኑ ወቅት ቅድምያ ሊሰጠዉ የሚገባዉ የንጹሐንን ሕይወት ማትረፍ ነዉ ። ይህን ስል የሁለቱን ፓርቲዎች ጥምረት ወይም ትብብርን ከቁም ነገር ሳልቆጥር መቅረቴ አይደለም። በቅድምያ ትኩረት ልns,ጠዉ የሚገባዉ ግን የድሆችን የንፁሐንን ሕይወት መታደግና ሰላም ማስፈን ነዉ።

በጣም ጥሩ ጅምር ስለሆነ ሌሎችም አርአያነታቸዉን ቢከተሉ ሲሉ በዚህ በማኅበራዊ መገናኛ ሃይሉ ጎፍሪ የተባሉ የ«DW» ተከታታይ የሰጡት ምክር ነዉ።

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሠ


ተዛማጅ ዘገባዎች

ተከታተሉን