1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

    ጣሊያን የሚያስገባዉ አደገኛዉ መንገድ

ሰኞ፣ ግንቦት 21 2009

በሕገወጥ ሰዉ አሸጋጋሪዎች አማካኝነት ወደ ጣሊያን ለመግባት የሜዲትራኒያን ባህርን በአደገኛ ሁኔታ እንዲያቋርጡ በየጊዜዉ ቁጥራቸዉ እጅግ የበረከተ ተሰዳጆች ይላካሉ። እነሱን የጫኑት አብዛኞቹ ጀልባዎች ደግሞ የሚነሱት ከሊቢያ ወደብ ነዉ። ተሰዳጆቹም ከተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት የሚመጡ ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/2dn5v
Reportagebuch Bilal
ምስል Verlag Antje Kunstmann

Gefährlicher Weg nach Italien - MP3-Stereo

ከሚሰደዱባቸዉ መንገዶች አንዱ በኒዠር በኩል የሚያቋርጥ ሲሆን ሜዲትራኒያን ባህርን ለመሻገር ከሚጠቀሙባቸዉ ጀልባ ተብዬዎች ያልተናነሰ አደገኛ መስመር እንደሆነ ነዉ የተገለጸዉ።

Reportagebuch Bilal
ምስል Verlag Antje Kunstmann

አጋዴስ የማዕከላዊ ኒዠር ዋና ከተማ ናት። ይህ ደግሞ አዉቶቡስ መናኸሪያዉ ነዉ። ብዙዉን ጊዜ በረሃዉን አቅርጠዉ ወደሊቢያ ለመሻገር የሚፈልጉ መንገደኞችን የጫኑ አዉቶቡሶች ወደዚህ የአዉቶቡስ ማቆሚያ ስፍራ ይመጣሉ። በሕገወጥ መንገድ ከሀገር ወደ ሀገር አሸጋጋሪዎቹ ረዳቶች በዚህ ስፍራ ጉዟቸዉን የሚያቀናጅላቸዉ የሚፈልጉትን ተሰዳጆቹን የሚያገኙት። ከአሸጋጋሪዎቹ አንዱ፤

«ተሰዳጆቹ ከጋና፣ ናይጀሪያ፣ ሶማሊያ፤ ከተለያዩ ከአጋዴስ እጅግ ከራቁ የአፍሪቃ ሃገራት ነዉ ወደዚህ የሚመጡት። ከየተነሱበት በኒያሚ አድርገዉ አጋዴስ ይገባሉ። ሲጓዙም ከደንበኞቻችን ጋር እየተገናኙ መንገድ የሚመሩ ሰዎች አሉን። እኛ /የንግድ/ የቢዝነስ ሰዎች ነን።»

ተሰዳጆቹን በቴኔሬ በረሃ አቋርጠዉ ሊቢያ እንዲገቡ የሚያጓጉዙት የንግድ ሰዎች ጠቀም ያለ ገንዘብ ያገኛሉ። ኒዠር ወደአዉሮጳ ለመግባት ለሚሞክሩ ተሰዳጆች መሸጋገሪያ ሀገር ሆናለች። ኒዠንር አቋርጦ ለሚጓጓዘዉ ተሽከርካሪ ደግሞ መነኻሪያዋ የበረሃ ከተማ አጋዴስ ናት።

አትሞ ሕገወጥ ሰዉ አሸጋጋሪዎቹ ስለጉዞዉ በፈቃደኝነት ቪዲዮ ያሳያሉ። አንደኛዉ ቪዲዮ በርካታ ፒካፕ ተሽከርካሪዎች የማንም ባልሆነዉ ግዛት ዉስጥ ሲጓዙ ያሳያል። ጎማ መቀየር አለበት። ፊልሙን በሞባይሉ የቀረጸዉ ከሹፌሮቹ አንዱ አንዱ እንዲህ ይላል።

Niger Agadez Bild 1 Konvoi mit Migranten verlässt Agadez
ምስል DW/A. Kriesch/J.-P. Scholz

«ከፊት ለፊታችን በመንገዳችን ላይ ወታደሮች እንዳሉ ተነግሮናል። እናም በግማሽ ሰዓት ዉስጥ ጉዟችንን እንጀምራለን።»

የናይጀሪያ ወታደሮች እነዚህን ሰዎች ከመንገዱ ላይ ሊያስወግዷቸዉ ይፈልጋሉ። በሚሳፈሩበት አካባቢ እጅግ በርካታ ተሰዳጆ ች ስብስብ ብለዉ ይገኛሉ። እያንዳንዳቸዉ 300 ዩሮ ከፍለዋል። ሕገወጥ አሸጋጋሪዎቹ ከበረሃ ከተማዋ አጋድሲ ተነስተዉ የቴኔሬን በረሃ በማቋረጥ ከሊቢያዋ ሰብሃ ይደርሳሉ። በአዉሮጳ ኅብረት ማሳሰቢያ የኒዠር መንግሥት ይህን ጉዞ አግዷል። አዴስ ላይ የእስራት ርምጃም ተወስዷል። በርካታ ትላልቅ ተሽከርካሪዎችም ተወርሰዋል። በዚህ ምክንያትም ከዚያ ወዲህ በአጋዴስ በኩል ብዙም ተሰዳጆች በይፋ መምጣት ትተዋል። እንቅስቃሴዉ ግን ቀጥሏል። ሕገወጥ አሸጋጋሪዎቹ በበረሃዉ ዉስጥ ሌላ መንገድ ቀይሰዋል። በዚህኛዉ መስመር ጉዞዉ ረዘም ያለ ሰዓት ስለሚወስድ ተሰዳጆ ከፍ ያለ ገንዘብ መክፈል ይጠበቅባቸዋል ይላሉ ኒዠር የሚገኘዉ የዓለም የስደተኞች ድርጅት IMO ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጁዜፔ ሎፕሬቴ። በርካታ ተሰዳጆች በአደገኛዉ ጉዞ ምክንያት ሜዲትራኒያን ባህር ዉስጥ እየሞቱ ቢሆንም አሁንም ብዙዎች በረሃዉን እያቋረጡ ወደዚያዉ መጓዛቸዉን ቀጥለዋል።

«በጎርጎሪዮሳዊዉ 2015ዓ,ም ሜዲትራኒያን ባህር ዉስጥ 5000 ሰዎች ሰጥመዉ ሞተዋል። በረሃ ዉስጥ የሞቱት ደግሞ የዚህ ሦስት እጅ እጥፍ ይሆናል ተብሎ ይገመታል።»

የበረሃዉን ጉዞ መቋቋም የሚችል ሊቢያ መግባቱ ይሳካለታል። ሆኖም እዚያ የሚደርሱ ተሰዳጆች የሚገጥማቸዉን ይህች ሴት እንዲህ ትገልጸዋለች።

«ወደመጠለያችን እና ወደምንሠራበት ስፍራ መጡ። ከዚያም ያለንን ሁሉ ወሰዱ።»

Flüchtlinge in Lybien
ምስል DW/Karlos Zurutuza

ታማኝ የመረጃ ምንጮች እንደሚሉት ሊቢያ ዉስጥ ስደተኞች መሠረታዊ ነገሮችን በማጣት ይሰቃያሉ፣ ይበዘበዛሉ እንዲሁም ገንዘብ እንዲያመጡ ጫና ይደረግባቸዋል። አንዳንዶቹም ቤተሰቦቻቸዉ ካሉበት ገንዘብ እንዲሰጡ ስቃይ ይፈጸምባቸዋል። የተረፉት እና ገንዘብ ያላቸዉ ተሰዳጆች በእነዚያ ለባህር ጉዞ አስጊ በሆኑ ጀልባዎች ተጭነዉ ይላካሉ። አብዛኞቹ ጀልባዎች እጅግ አደገኞ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ናቸዉ። እነሱ የሚገጥማቸዉን አሰቃቂ እጣ ፈንታም ከአደጋዉ ሊያድኗቸዉ የሚሞክሩት ወገኖች በፊልም ይቀርጹታል። IOM በኒዠር በረሃ እና ሜዲትራኒያን ባህር ላይ ተሰዳጆች ስለሚገጥማቸዉ አደጋ የሚያሳይ ፊልም በኢንተርኔት ይፋ አድርጓል። እንዲያም ሆኖ ሊቢያ ዉስጥ የሚገኘዉ ወደአዉሮጳ ለመሰደድ የቋመጠ ይህ ሰዉ ይህን ጉዞ ራሴዉ ልሞክረዉ ነዉ የሚለዉ።

«እግዚአብሔርን አምናለሁ። ከኒያሚ እዚህ ድረስ አምጥቶኛል። ወደላምፔዱዛም ፈጣሪ ሊያደርሰኝ ይችላል።» 

የንስ ቦርኸርስ/ ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ