1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጤዛ ፊልም እያሸነፈ ነው

እሑድ፣ መጋቢት 6 2001

“ጤዛ” የተሰኘውና በደርግ ዘመን ዙሪያ የሚያጠነጥነው ይህ ፊልም በአሁኑ ሠዓት ኢትዮጵያ ውስጥ በእይታ ላይ እንዳለ ወ/ሮ ሰሎሜ ገሪማ ገልፀዋል። መሰል ፊልሞች በእንደነዚህ አይነት ታላላቅ መድረኮች ላይ ማሸነፋችው ሌሎች ብቅ ብቅ እያሉ የሚገኙና ተስፋ የሚጣልባቸው የሀገራችን የፊልም ባለሙያዎችን የበለጠ ማነቃቃቱ አይቀርም።

https://p.dw.com/p/HCVX
“ጤዛ” በሽልማቶች ተንበሽብሿል
“ጤዛ” በሽልማቶች ተንበሽብሿል
“ጤዛ” ከቡርኪናፋሶ ፊልም ፌስቲቯል በተጨማሪ እንዲሁ በተለያዩ ሽልማቶችም ተንበሽብሿል። ከነዚህም መካከል በቅርቡ ድህነትን በመዋጋት በሚል የተባበሩት መንግስታት ሽልማትን፣ በወጥነቱ፤፣ በቴክኒክ ጥራቱ፣ በአተዋወን ስልቱ ደግሞ የዛይን ሽልማት ተቀዳጅቷል። የሮተርዳም ፊልም ፌስቲቯል የዲዮራፍቴ ሽልማትን፣ በቬኒስ ፊልም ፌስቲቫል ምርጥ የፊልም ፅሁፍ በሚል በዳኞች የልዩ ሽልማት ባለቤት ሊሆን ችሏል። ከዚህም በተጨማሪ ፊልሙ በቱኒዚያ ፊልም ፌስቲቫል በምርጥ ሙዚቃ፣ በምርጥ cinematography እና በምርጥ የወንድ ደጋፊ ተዋንያን ሲያሸንፍ፤ በፈረንሳይ ዓለም አቀፍ ፊልም ፌስቲቫል፤ ምርጥ ፊቸር ፊልም በሚል የወርቅ ተሸላሚ ሆኗል። በቬኔዙዌላ የአማዞንያን ፊልም አዋርድ እና የግሪክ ቴሳሎኒኪ ፊልም ፌስቲቫል ለሰብዓዊነት ዋጋ በመስጠት በሚል ሽልማቱን ጠቅልሎ ወስዷል።