1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጸረ ሽብሩ ትግል እና አጠያያቂው የፓኪስታን ሚና

ሐሙስ፣ ነሐሴ 5 2003

የአልቃይዳ መሪ ኦሳማ ቢንላድን ለአመታት በፓኪስታን ተሸሽገው ነበር። ያ ደግሞ ፓኪስታን ተስፋ የሚጣልባት የምዕራኖች ወዳጅ ስለመሆኗ ጥያቄ አስነስቷል።

https://p.dw.com/p/RfGT
ምስል AP/DW

በፓኪስታንና በዩ ኤስ አሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት ተለዋዋጭ ነው። እኢአ በ1980ቹ ኢስላማባድና ዋሽንግተን ጥብቅ ግንኙነት ነበራቸው ያም የቀዩ ጦር 1988/89 ዓም አፍጋኒስታንን ለቆ እስኪወጣ ድረስ ዘልቋል። ኃላም የአሜሪካ ፍላጎት ይቀዘቅዛል። እኢአ ከመስከረም 1 2001 ጀምሮ ዮ ኤስ አሜሪካ በፓኪስታን ላይ መልሳ ትኩረቷን ትጥላለች። ፓኪስታን ከአልቃይዳና ከታሊባን ጋር ባለው ትግልም ስንቅ ማቀበያ ትሆናለች። ምንም እንኳን ፓኪስታን ስምምነቱን ብትቀበልም በሙሉ ልብ አልነበረም፤ ምክንያቱም ኢስላማባድ ከታሊባን መንግስት ጋር ጥሩ ግንኙነት ነበረውና። አሁንም ቢሆን ከጎረቤት አገሪቷ ጋር ምጣኔ ሀብታዊ ግንኙነት አላት።

« የፓኪስታን ሌላው ፍላጎት «ጥልቃዊ ኢላማ» ተብሎ የሚጠራውን አፍጋኒስታን ላይ ማኖር ነው። ለፓኪስታን ወሳኙ ነገር አፍጋኒስታን ውስጥ የፓኪስታንን ፍላጎት የሚጠብቅ መንግስት መፍጠር ነበር።» ይላሉ የደቡብ እስያ ተንታኝ ኮንራድ ሼተር። ፓኪስታን ለዚህ ስትል ነው ሙሉ ኃይሏን ታሊባን ላይ የማታውለው ይላሉ። አፍጋኒስታን ውስጥ «ጥልቅ ኢላማ» ሲባል- አንድ ቀን ዳግም ከህንድ ጋር ጦርነት ከተከፈተ ለፓኪስታን ጦር የሚሆን ምሽግ ነው። ። በሁለቱ አገራት መካከል እስካሁን ሶስት ጦርነቶች ተካሂደዋል። የድንበር ግጭቶቹ እስካሁን ለአስርተ አመታት እልባት አላገኙም።

በህንድ ላይ አድማ ፈጣሪዎች

Dreiergipfel Washington
ምስል AP

የኢስላማባድ ወቅታዊ ኢላማ፤ ጠምካራ የአክራሪ ኃይሎችን ማሰባሰብ ነው ይላሉ የፓኪስታን አሸባሪዎች ላይ ተመራማሪ -ራሂሙላህ ዩሱፍዛይ።ህንድ ይበልጡን የሙስሊም አገር ስላልሆነች አክራሪዎች በሙሉ የህንድ ተቃዋሚ ይሆናሉ ብላ ነው ፓኪስታን የምታምነው ። ዳግም ከህንድ ጋር ጦርነት ቢነሳ ኢስላማባድ አፍጋኒስታን ውስጥ ተባባሪ ያስፈልጋታል። ታሊባን ሂንዱኩሽ ላይ ማምለኪያ ቦታዎችን መስራት ማቀዷ፤ ከፓሲስታን አላማ ጋር ተስማሚ ነው። « በፓኪስታን በ ዮ ኤስ አሜሪካና በተቀሩት ምዕራብ አገሮች መካከል ያለው አለመስማማት የታሊባን የፖለቲካ አካሄድን ይመለከታል። ፓኪስታን ፖለቲካዊ መፍትሄ አቅርባ ከታሊባን ጋር መደራደር ነው የምትፈልገው። በተጨማሪም ፓኪስታን በዚህ ድርድር ላይ ዋና ሚና መጫወት ትፈልጋለች። ዮ ኤስ አሜሪካ ደግሞ እንደ በፊቱ ማሸነፍ ነው የምትፈልገው» ይላሉ ዩሱፍዛይ።

የዮ ኤስ አሜሪካ ፍላጎት

Karte Pakistan mit Waziristan

የ ዮኤስ አሜሪካ መንግስትም ቀስ በቀስ በድርድር እየሞከረ ነው። ከዚያ በፊት ግን ታሊባኖች ከአሸባሪው አል ቃይዳ እራሳቸውን ነፃ ማድረግ አለባቸው። አፍጋኒስታን ያሉ 100000 የአሜሪካ ወታደሮች ታሊባንን ለድርድር ማሳመን ይኖርባቸዋል። የፓኪስታን አክራሪ ምሽጎች ላይ ጠንካራ የማስፈራሪያ ዛቻ ማድረጉ አንዱ የዮ ኤስ አሜሪካ ዘዴ ነው። የአሜሪካ መልዕክት ግልፅ ነው፤ በፓኪስታን እና በአሸባሪዎቹ መካከል ያለ የትብብር ስራ ተቀባይነት አይኖረውም። እንደ ፖለቲካ ተንታኝ ዮህን ሂፕለር አመለካከት መልዕክቱ እንደውም አንዳንድ የኢስላማባድ የመንግስት ተወካዮች ዘንድ ደርሷል። « ፓኪስታን ውስጥ ባለፉት አመታት አብዛኞቹ የጥቃቱ ሰለባ ሊሆኑ የቻሉበት ምክንያቱ የአፍጋኒስታን ጦርነት በከፊሉ በአገራቸው ላይ መልሶ ጉዳት በመፍጠሩ ነው። አፍጋኒስታንን ያልተረጋጋች አገር ማድረግ ወደፊት ለፓኪስታን ጉዳት እንጂ ጥቅም አያመጣም።»

ይሁንና ተንታኞች ስጋት አላቸው። የፓኪስታን መንግስት ሀሳቡን ባንዴ ይቀይር ይሆናል ብለው ያምናሉ። የፓኪስታን ወታደር ጠንካራ ነው። የስላይ ቡድኑም ቢሆን ወሳኝ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ አገሪቷ በቢሊዮን የሚቆጠር የአሜሪካ እርዳታ እንዲቀርባት አስፈልግም። ስለዚህ የኢስላማባድ መንግስት ከባድ የሆነ ስራ እያካሄደ ነው። ባንድ በኩል የአክራሪ ኃይሎቹን ደህንነት ለመጠበቅ ይሞክራል በሌላ በኩል ደግሞ ደግሞ ከ ዮ ኤስ መንግስት ጋር ያለውን ትብብር ማቆየት ይሻል- እንደ ተንታኞቹ አመለካከት።

አስቸጋሪ አጋርነት

Pakistan Islamisten Trainingslager an der Grenze zu Afghanistan
ምስል AP

ፓኪስታን ሀሳቧን እስትክትቀይር አሜሪካ ብዙ ትዕግስት ሊኖራት ያስፈልጋል ይላሉ። ሄኒግ ሪከ። በጀርመን የውጭ ፖለቲካ ማህበር ውስጥ የዮ ኤስ አሜሪካ ተንታኝ ናቸው። እንደሳቸው የ ዮ ኤስ መንግስት ምንም አይነት አማራጭ አላቀረበም። « አሜሪካኖች ፓኪስታን ላይ ይበልጥ ጫና እየተጠወሙ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የሚያደርጉት ጫና በዚሁ ከቀጠለ ጠንካራ ያልሆነው የኢስላማባድ መንግስት የሚይዝ የሚጨብጠውን ያጣል። ያኔ ጉዳቱ ያመዘነነ ነው የሚሆነው። የሙስሊም ኃይሎች ይጠናከራሉ።» ያን ደግሞ እንደ ሪከ እምነት፤ የአሜሪካ ፍላጎት አይደለም።

ታድያ ፍላጎታቸው ይለያይ እንጂ ዋሽንግተንና ኢስላማባድ በየፊናቸው ከታሊባን እና ከአልቃይዳ ጋር አፍጋኒስታን ውስጥ ትግል ይዘዋል። ያም ሆኖ በአስቸጋሪው የትብብር ስራ አንዱ የሌላኛው ጥገኛ ሆነው ይቆያሉ።

ራትቢል ሻሚል

ልደት አበበ