1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጽጌረዳዉ ሰኞ በኮሎኝ

ሰኞ፣ የካቲት 16 2001

በየዓመቱ የካርኒቫልን በዓል ማክበር በተለይ ለኮሎኝ ከተማ ልዩ ድምቀት ይፈጥርላታል። የበዓሉ ታዳሚዎች ምንም እንኳን በአብዛኛዉ የበዓሉ የትመጣና ምክንያት ባያዉቁም፤ በሚወዷቸዉ የተለያዩ አለባበሶች ራሳቸዉን አስዉበዉ በቀለማት ፊታቸዉን አዝጎርጉረዉ ብቅ ይላሉ።

https://p.dw.com/p/GznK
...ክንፍ ለኦባማ...
...ክንፍ ለኦባማ...ምስል AP

ለበዓሉ የሚደረገዉ ዝግጅት ለገናም ሆነ ፋሲካ ከሚደረገዉ አይተናነስም ማለት ይቻላል፤ ከልብስ ዝግጅቶች አንስቶ መጠጥ ሁሉ በዓይነት በዓይነቱ ተስተካክሎ በየገበያ አዳርሾች በማስታወቂያ ታጅቦ ይቀርባል። ሃይማኖታዊ ዳራ እንዳለዉ የሚናገሩ የእምነት ሰዎችም አሉ። ለዓብይ ፆም እንደመዳረሻ የሚቀርብ በመሆኑም፤ ረቡዕ ዕለት በካቶሊክ ቤተክርስቲያን የዚሁ ቀጣይ ዝግጅት ይኖራል፤ ርኩስ መንፈስን የማቃጠል። የዛሬ ሳምንት ሰኞ ታዲያ ፆም ለጿሚዎቹ ይጀመራል።