1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፀሀፊ ዳዊት ግዛው

እሑድ፣ ሰኔ 23 2011

አሁንም ሆነ በፊትም የሚጽፈው ለገንዘብ ሳይሆን የስነ ጽሁፍ ጥሙን ለማርካት መሆኑን የሚናገረው ዳዊት ከአሁን በኋላ የግጥም መፀሀፍ ለማሳተም አያስብም። ተጽፈው የተቀመጡ ሌሎች ድርሰቶቹን ግን በቅርቡ የማሳተም እቅድ አለው።

https://p.dw.com/p/3KvRc
Dawit Gizaw | Autor aus Äthiopien
ምስል privat

ፀሀፊ ዳዊት ግዛው

የሰለጠነበት እና የተሰማራበት ሞያ የኤሌክትሪክ ምህድስና ነው።ከርሱ ጎን ለጎን ደግሞ ይገጥማል ይጽፋል።ግጥሞቹንና እና አጫጭር ወጎቹን ያካተተበትን የመጀመሪያ መጸሀፉን በዚህ ዓመት  ለህትመት አብቅቷል። ለህትመት የተዘጋጁ ሌሎች ያልታተሙ የስነ ጽሁፍ ሥራዎችም አሉት፤የኤሌክትሪክ መሐንዲስ እና ጸሀፊ ዳዊት ግዛው።ትውልዱ እና እድገቱ ሐረር ለሆነው፣ ለዳዊት  ስነ ጽሁፍ የታመቀን ስሜት ማውጫ ማስተንፈሻ ነው።ዳዊት እንደሚለው ከሥራው ጎን ለጎን ለሚያካሂደው የስነ ጽሁፍ ሥራ መሠረቱ የሐረሩ የልዑል ራስ መኮንን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ብራና የኪነጥበብ ማዕከል ነው።ከርሱ የቀደሙት የማዕከሉ አባላት የስነ ጽሁፍ ፍቅሩ ይበልጥ እንዲጨምር እና ይበልጡን ወደ ዘርፉ እንዲሳብ ምክንያት ሆኑኝ ይላል።ለስነ ጽሁፍ የላቀ ፍቅር እንዳለው የሚናገረው ዳዊት የተማረው የኤሌክትሪክ ምህድስና መሆኑ እና በዚሁም ሞያ መሰማራቱ ታዲያ ለምን የሚለውን ጥያቄ ማጫሩ አይቀርም።ሰው በተሰኘውና ወደ 72 የሚሆኑ ግጥሞችን እና 5 ወጎችን በያዘው ባለ 105 ገጹ የዳዊት ግዛው መፀሀፍ «ኢትዮጵያ» እንደተባለው ግጥም ሁሉ ሌሎችም ሰው እና ሰውነት ላይ ያተኮሩ ግጥሞችም አሉ።ከመካከላቸው አንዱ «ፍሬ አልባ ማገዶ»የሚል ርዕስ የሰጠው ግጥሙ ነው። አሁንም ሆነ በፊትም የሚጽፈው ለገንዘብ ሳይሆን የስነ ጽሁፍ ጥሙን ለማርካት መሆኑን የሚናገረው ዳዊት ከአሁን በኋላ የግጥም መፀሀፍ ለማሳተም አያስብም። ተጽፈው የተቀመጡ ሌሎች ድርሰቶቹን ግን በቅርቡ የማሳተም እቅድ አለው።

Buchcover | "Sew" von Dawit Gizaw

ሙሉውን ዝግጅት ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ።

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ