1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፀረ-የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ ቀን

ዓርብ፣ ሰኔ 5 2007

ድርጅቱ ዛሬ የሚታሰበውን ፀረ የህፃናት ብዝበዛ ቀን ምክንያት በማድረግ ባወጣው ዘገባ ከዓለማችን ህፃናት አንድ አራተኛው በዘመናዊ ባርነት ውስጥ እንደሚገኙ ገልጿል ። 5 ሚሊዮን ያህሉ ከባርነት ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖሩም ጠቁሟል ።

https://p.dw.com/p/1FgNm
Kinder in indischen Steinbrüchen
ምስል picture-alliance/dpa

[No title]


ለአቅመ አዳምና ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ በርካታ ሕጻናት በአብዛኛው የዓለም ክፍል ለተለያዩ የጉልበት ብዝበዛዎች ይዳረጋሉ።በአሁኑ ጊዜ በዓለማችን ቁጥራቸው ከ160 ሚሊዮን በላይ የሚገመት ህፃናት ትምህርት ቤት ሳይሄዱ በጉልበት ሥራ ተሰማርተው ራሳቸውንና ወላጆቻቸውን እንደሚረዱ ዓለም ዓቀፉ የሠራተኛ ማህበር ILO አስታውቋል ። ድርጅቱ ዛሬ የሚታሰበውን ፀረ የህፃናት ብዝበዛ ቀን ምክንያት በማድረግ ባወጣው ዘገባ ከዓለማችን ህፃናት አንድ አራተኛው በዘመናዊ ባርነት ውስጥ እንደሚገኙ ገልጿል ። 5 ሚሊዮን ያህሉ ከባርነት ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖሩም ጠቁሟል ። በዘገባው እንደተጠቀሰው በእስያና በፓስፊክ አካባቢዎች 78 ሚሊዮን ህፃናት፣ ከሰሃራ በስተደቡብ ባሉ የአፍሪቃ ሃገራት ከሚገኙ ህፃናት ደግሞ 21 በመቶው ወይም 59 ሚሊዮኑ በጉልበት ሥራ ተሰማርተዋል ።ፀረ-የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ ቀን ምክንያት በማድረግ ከሄለ የፕሰን የቀረበውን ዘገባ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል አጠናቅሮታል ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ