1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፈላሻሙራን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ለማስገባት የሚደረገው ሙከራ

ሰኞ፣ ሐምሌ 13 2001

ኢትዮጵያ የሚገኙ የአይሁድ ዝርያ አለን የሚሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ እስራኤል ለመፍለስ ያስገቡትን ማመልከቻ የሚመረምሩ ባለስልጣናትን እስራኤል ባለፈው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ ልካለች ።

https://p.dw.com/p/ItMr
ምስል picture-alliance / dpa

ኢትዮጵያ ውስጥ ክርስቲያን እንድንሆን የተገደድን ቤተ እስራኤላውያን ነን የሚሉት እነዚሁ አመልካቾች በጊዜያዊ መጠለያዎች ውስጥ ሆነው ወደ እስራኤል ለመጓዝ በመጠባበቅ ላይ ናቸው ። እ.ጎ.አ ከ1980 እስከ 1990 ዎቹ ዓመታት ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የተወሰዱ ወደ አንድ መቶ ሺህ የሚደርሱ ቤተ እስራኤላውያን እስራኤል ውስጥ ይኖራሉ ። ከዚያም በተለያዩ ጊዜያት በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላውያን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ሄደዋል ። ከዛሬ ሁለት አመት አንስቶ ግን ይህ ዓይነቱ ጉዞ ተቋርጧል ። ዜነነህ መኮንን ከእየሩሳሌም እንደዘገበው እስራኤል ቀደም ብለው የገቡት ቤተ እስራኤላውያኑን ፈላሻሙራ የተባሉትን ቀሪ ቤተ እስራኤላውያን ወደ እስራኤል የማምጣቱ ጥረት በመጓተቱ ቅሬታቸውን እያሰሙ ነው ።

ዜናነህ መኮንን/ሂሩት መለሰ/አርያም ተክሌ