1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኤርትራ እና የሱዳን ስደተኞች መካከል በተነሳ ፀብ በርካቶች ተጎዱ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 20 2012

በፈረንሳይ ካሌ በሚገኙ በኤርትራ እና በሱዳን ስደተኞች መካከል በተነሳ የእርስ በዕርስ ፀብ በርካታ ስደተኞች ተጎድተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የካሌ ፖሊስ አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3U1dN
Frankreich Calais - Flüchtlinge aus dem Sudan
ምስል picture-alliance/NurPhoto/G. Orenstein

በፈረንሳይ ካሌ በሚገኙ በኤርትራ እና በሱዳን ስደተኞች መካከል በተነሳ የእርስ በዕርስ ፀብ በርካታ ስደተኞች ተጎድተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የካሌ ፖሊስ አስታውቋል። ሰባት ሱዳናውያን እና ሁለት ኤርትራውያን ጉዳት እንደደረሰባቸውም ፖሊስ አስታውቋል። ስደተኞች ለጊዜው ተጠልለውበት በሚገኙ የካሌ አቅራቢያ ስፍራዎች ባለፈው ዕሮብ ምሽት ነበር ዱላ በያዙ ስደተኞች ፀብ የተቀሰቀሰው።  ፀቡም እስከ ሀሙስ ዘልቆ ነበር። ፖሊስም ሁኔታውን ለማረጋጋት ርምጃ መውሰዱን እና አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙን ገልጿል። በአራት ፀጥታ ማስከበር ተግባር ላይ የነበሩ ፖሊሶች ላይም ጉዳይ መድረሱ ተነግሯል። 


ሐይማኖት ጥሩነህ 
ልደት አበበ