1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፈረንሳይ፣ ብሪታንያ እና የስደተኞቹ መበራከት ያስከተለው ቀውስ

ሰኞ፣ ነሐሴ 18 2007

ወደ አውሮጳ የሚጎርፈው ስደተኛ ቁጥር ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ እያሻቀበ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ በሰሜን ፈረንሳይ የወደብ ከተማ ካሌ የሠፈሩ ተገን ጠያቂዎች ዩሮታነል በተባለው የባህር ዋሻ በኩል ለማለፍ ይሞክራሉ።

https://p.dw.com/p/1GKoY
Frankreich: Polizeieinsatz gegen Flüchtlinge in Calais am Eurotunnel
ምስል Getty Images/AFP

[No title]

ስደተኞቹ በዋሻው በሚያልፉት ባቡሮች ወይም የጭነት መኪኖች ውስጥ ተሸሽገዉ ወይም አንድ የሱዳን ስደተኛ እንዳደረገው በእግሩ ተጉዞ ወደ ብሪታንያ በሕገ ወጥ መንገድ ለመግባት የሚያደርጉት ሙከራ ባካባቢው አሳሳቢ ቀውስ ፈጥሮዋል። ብሪታንያ ስደተኞቹ ወደ ግዛትዋ እንዳይገቡ በፈረንሳይ ላይ ከፍተኛ ግፊት አሳርፋለች።

በፈረንሳይ እና ብሪታንያ ስለሚታየው የስደተኞች እንቅስቃሴ፣ በዚሁ አንፃር ምን እየተደረገ ይገኛል? ስለዚሁ ጉዳይ የፓሪሷን ወኪላችን ሀይማኖት ጥሩነህ እና የለንደኗን ወኪላችን ሀና ደምሴን በስልክ አነጋግረናል።

ሀይማኖት ጥሩነህ/ሀና ደምሴ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ