1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፈረንሳይ ወታደራዊ ስምምነቱን ስለማገዷ አስተያየት

ረቡዕ፣ ነሐሴ 12 2013

ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር የገባችዉን ወታደራዊ ትብብር ስምምነት ማገዷን ባሳለፍነው ሳምንት የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት (AFP) ዘግቧል። ፈረንሳይ የወሰደችው አቋም አንድምታው እንዴት ይታያል፤ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ወዴት አቅጣጫ ሊያመራ ይችላል በሚሉ ጉዳዮች ላይ የፈረንሳይ  ምሑራን እና የቀድሞ የፈረንሳይ ዲፕሎማት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

https://p.dw.com/p/3z8Hk
Äthiopien und Frankreich unterzeichnen in Addis Abeba ein Abkommen
ምስል Getty Images/AFP/L. Marin

የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ወዴት አቅጣጫ ሊያመራ ይችላል?

ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር የገባችዉን ወታደራዊ ትብብር ስምምነት ማገዷን ባሳለፍነው ሳምንት የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት (AFP) ዘግቧል። እንደዘገባው ከኾነ  መጋቢት 2019 በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና በፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮ መካከል የተደረሰዉ ስምምነት ሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ ታግዷል። ኢትዮጵያ የባሕር ኃይል የመገንባት ፍላጎቷን ለመደገፍ ፈረንሳይ 85 ሚሊዮን ዩሮ (100 ሚሊዮን ዶላር) ብድርን የምትሰጥበት ስምምነት በሁለቱ ሃገራት መካከል ተፈጽሞ እንደነበርም ተዘግቧል። ፈረንሳይ የወሰደችው አቋም አንድምታው እንዴት ይታያል፤ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ወዴት አቅጣጫ ሊያመራ ይችላል በሚሉ ጉዳዮች ላይ የፈረንሳይ  ምሑራን እና የቀድሞ የፈረንሳይ ዲፕሎማት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። 

ሃይማኖት ጥሩነህ

ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ