1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፊልሞች ለአንድ ሀገር ባህል ያላቸው አስተዋፅዎ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 17 2004

ፊልም የአንድን ማህበረሰብ ባህል ለማንፀባረቅ ለማዳበር እና በአወንታዊም ይሁን አሉታዊ ጎኑ ለመለወጥ የሚረዳ የኪነ ጥበብ ዘርፍ ነው።

https://p.dw.com/p/15vbM
30.08.2008 kultrur 21 haile gerima
ምስል DW-TV

በዮናይትድ እስቴትስ ዋሽንግተን ዲሲ - ሀዋርድ ዮንቨርሲቲ ፕሮፌሰር እና ፊልም ሰሪ፤ ኃይሌ ገሪማ የዛሬው የባህል መድረክ እንግዳችን ነው ።  ሳንኮፋ፣ አድዋ፣ጤዛ የመሳሰሉ ፊልሞችን በመስራት ኃይሌ ገሪማ ይታወቃል። ባህል በአንድ ፊልም እንዴት ይገለፃል? የተለያዩ አላባዎችን እንደ ምሳሌ ጠቅሶልናል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ ከጣሊያን ወረራ በኋላ ፊልም እንደተስፋፉ እና በዘመኑ የነበሩ ወጣቶችም ከነዚህ ፊልሞች ትምህርት ሊቀስሙ እንደቻሉ ኃይሌ ገሪማ ያስረዳል።

የኢትዮጵያ ፊልሞች መሰራት ከተጀመሩበት አንስቶ እስካሁን ለኢትዮጵያ የባህል እድገት ምን አይነት አስተዋፅዎ እንዳደረጉ ከማውራታችን በፊት ኢትዮጵያ የሚሰሩ ፊልሞችን መመርመር ይገባናል ይላል ኃይሌ። «ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ጀርመን እና እንግሊዝ የመሳሰሉትም አገሮች ሲኒማ አለን ማለት አይችሉም» ይላል ኃይሌ። እንደምክንያት የጠቀሰው ፊልም የመስራት ኃይል ይጎድላቸዋል የሚል ነው።

Äthiopien/D 2008, R: Haile Gerima, Da: Aaron Arefe, Aby Tedla, 140 min Fotorechte auch hier: Filmmuseum Frankfurt / Main
ጤዛ፤ በኢትዮጵያ በተለይም በደርግ ስርዓት ላይ ያተኮረ የኃይሌ ገሪማ ፊልም ነው።ምስል Deutsches Filmmuseum Frankfurt am Main

አንድ ፊልም የአንድን ሀገር ባህል ለማንፀባረቅ መለስተኛ ሚና ነው የሚኖረው እንደ ኃይሌ ማብራሪያ። የኢትዮጵያ የፊልም ስራዎች ከፍተኛ ደረጃን ያልጠበቁ እንደሆነ ግልፅ ነው። ሆኖም በከፊልም ቢሆን መሻሻል ይታያል።  ይበልጥ  ባለሙያዎቹም ይሁኑ ገና ወደ ፊልም ስራው እየገቡ ያሉት፤ የፊልም ስራን ባህል ለማሳደግ ምን ማድረግ ይገባቸዋል?

አንዳንድ ፊልሞች ወደ ገበያ የሚወጡት ታሪኩ በተፈፀመበት ወቅት ሳይሆን የህዝቡ ጥያቄዎች በትክክልም ሆነ በስህተት መልስ ካገኙ በኋላ ነው። በርዕስ አመራረጥ ላይ ፓለቲካ ምን ያህል ተፅዕኖ አለው?  ኃይሌን የራሱን የፊልም ስራዎች እንደምሳሌ ወስዶ ያብራራልን አለ።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ