ፊደል ካስትሮ በ90 ዓመታቸው አረፉ

የቀድሞው የኩባ ፕሬዝዳንት እና አብዮታዊው ፊደል ካስትሮ በ90 ዓመታቸው ኩባ መዲና ሐቫና ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የቀድሞው የኩባ ፕሬዝዳንት እና አብዮታዊው ፊደል ካስትሮ በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ኩባን በፕሬዝዳንትነት የሚመሩት ታናሽ ወንድማቸው ራውል ካስትሮ ዜና ረፍታቸውን በአገራቸው ብሔራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ ዛሬ ይፋ አድርገዋል። ኩባም እስከ ኅዳር 25 ቀን 2009 ዓ.ም. የሚዘልቅ ብሔራዊ ሐዘን አውጃለች።

ፊደል ካስትሮ በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ወታደሮቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ እና አንጎላ በማዝመት ከአብዮታዊ ጓዶቻቸው ጎን ተሰልፈው አዋግተዋል። የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ለገነቡት ከፍተኛ የጦር ሰራዊት ድጋፍ አድርገዋል።

ለ47 አመታት ኩባን የመሩት እና አስር የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንቶች ሲፈራረቁ የታዘቡት ካስትሮ በጤና መታወክ ምክንያት መንበረ ስልጣናቸውን ለታናሽ ወንድማቸው ራውል ካስትሮ ያስረከቡት ከአስር አመት በፊት ነበር። 
 

እሸቴ በቀለ

ማንተጋፍቶት ስለሺ